የዲስክ መንሸራተት። መንስኤዎች እና ህክምና።
Author: admin
Date: 2021-09-06
#የዲስክ መንሸራተት። መንስኤዎች እና ህክምና።
#ቅዱስሚካኤልየባህልህክምና
#ሀኪምሰለሞንአዳሙ
#share
#like
01/13/2013
የዲስክ መንሸራተት በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት ህመም ሲሆን ከፍተኛ የህመም ስሜት እና ድካም የሚፈጥር ችግር ነው።
አንዳንድ ግዜ በእጅ ላይ የመደንዘዝ እና የድካም ስሜት ይፈጠራል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ በተቃራኒው ምንም ስሜት አይኖረውም። ዲስኩ የነካው ነርቭ ከሌለ የህመም ስሜት አይሰማንም።
የዲስክ መንሸራተት ምልክቶች ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ በራሳቸው ግዜ ሊጠፉ ይችላሉ። የህመም ስሜቱ የሚዘልቅ ከሆነ ግን ቀዶ ጥገና ማከናወን ሊኖረን ይችላል።
በዚህ ጽሁፍ የዲስክ መንሸራተት ምልክቶችን፣ ህክምና እና የቅድመ ጥንቃቄ መንገዶች እንዳስሳለን።
ህክምና
የዲስክ መንሸራተት ከፍተኛ የህመም ስሜት ሊፈጥር ይችላል። ነገር ግን ተገቢውን ህክምና በማድረግ ስሜቱን ማስታገስ እንችላለን።
የዲስክ መንሸራተት የሚያጋጥማቸው አብዛኞ ሰዎች በ4 ሳምንት ውስጥ ያገግማሉ።
የህመም ስሜት ከሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች በመቆጠብ እና የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ እንዲሁም የህመም መድሃኒቶችን በመውሰድ ህመሙን ማስታገስ እንችላለን።
መድሃኒቶች
የህመም ክኒኖች፡ እንደ ኢቡፕሮፊን(Ibuprofen) አይነት የህመም መድሃኒቶችን በመውሰድ የህመም ስሜትን በተወሰነ ደረጃ መቀነስ ይቻላል
የነርቭ መድሃኒቶች፡ ጋባፔንቲን(gabapentin)፣ ፕሬጋባሊን(pregabalin) እና ዱሎክሴቲን(duloxetine) የመሳሰሉ መድሃኒቶች የነርቭ ህመምን ለማስታገስ ይረዳሉ
ናርኮቲክስ፡ የህመም መድሃኒቶች የህመም ስሜቱን ማስታገስ ካልቻሉ ኮዲን(Codeine) ወይም ሌላ የናርኮቲክ መድሃኒቶች ይታዘዛሉ። ነገር ግን እነዚህ መድሃኒቶች ማቅለሽለሽ፣ ግራ መጋባት እና የሆድ ድርቀት ስሜቶችን ሊፈጥሩ ይችላሉ
በኮርቲዞን መወጋት፡ ህመሙ የተፈጠረበት ቦታ ላይ ኮርቲዞን በቀጥታ መወጋት የህመም ስሜቱን ሊቀንስ ይችላል። ነገር ግን ይህንን መድሃኒት አዘውትሮ መወጋት ሌላ የጤና መዘዝ ሊያመጣ ይችላል
የኢፒዱራል መርፌ(Epidural injections): ኢፒዱራል የተባለው የሰውነት አካል ላይ የሚደረግ መርፌ መወጋት ነው። መርፌው በውስጡ የተለያዩ ህመም ስሜትን የሚያስታግሱ መድሃኒቶች በውስጡ የያዘ ነው።
ጡንቻ የሚያላሉ መድሃኒቶች፡ እነዚህ መድሃኒቶች የጡንቻ መሳሳብን ይቀንሳሉ። ነገር ግን የማዞር ስሜት ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ቴራፒ
የሰውነት ቴራፒስቶች ህመሙን የሚቀንሱ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን ለማግኘት ይረዱናል።
ቴራፒስቶች ከሚከተሉት ማስታገሻዎች ውስጥ የተወሰነውን እንድንሞክር ይመክሩናል
በሙቀት ወይም በረዶ ማስታገስ
የአልትራሳውንድ ህክምና፡ የተጎዳውን ክፍል በአልትራሳውንድ ድምጽ በማከም የደም ዝውውር በተሻለ ሁኔታ እንዲካሄድ ማድረግ ይቻላል
ገመድ፣ ክብደት እና ፑሊ በመጠቀም የተጎዳው ቦታ ላይ ጫና መፍጠር
ለአጭር ግዜ አንገትን በብሬስ ማሰር
ኤሌክትሮቴራፒ፡ የኤሌክትሪክ ኢምፐልስ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የህመም ስሜትን ያስታግሳል
ቀዶ ጥገና
ከላይ የተጠቀሱት ህክምናዎች ህመሙን ማስታገስ ካልቻሉ፣ የመደንዘዝ ስሜቱ ከቀጠለ ወይም ሽንትን የመቆጣጠር ብቃት መውረዱን ከቀጠለ ቀዶ ጥገና ማድረግ ይመከራል።
በቀዶ ጥገናው ወቅት አብዛኛውን ግዜ ወጣ ያላው የዲስክ ክፍል በቻ ይወገዳል። ይህ ቀዶ ጥገና ኦፕን ዳይሴክቶሚ(Open disectomy) ይባላል። ብዙ ግዜ የላፓራስኮፒክ መንገድን በመጠቀም ይከናወናል። ሃኪሙ ሆድ ውስጥ ትንሽ ቀዳዳ ይክፍትና ሆድን አልፎ ጀርባ አጥንት ላይ ቀዶ ጥገና ያከናውናል።
በዚህ መንገድ ቀዶ ጥገና ማካሄድ የጀርባ አጥንት አካሎቶችን ከማስወገድ ያድናል። የጀርባ አጥንት ነርቮችም ሳይነካኩ ቀዶ ጥገናው ማከናወን ይችላል።
የተለመደ ባይሆንም አንዳንድ ግዜ ሙሉ ዲስኩ መወገድ ይኖርበታል። ዲስኩን አስወጥቶ በብረት በመተካት ቀዶ ጥገናው ይፈጸማል።
መንስኤዎች
የጀርባ አጥንት ቨርተብሬ የሚባሉ የ26 አጥንቶች ስብስብ ነው። በቨርተብሬዎች መሃከል የሚገኙ ርብራብ መሰል ክፍሎች ናቸው የጀርባ አጥንት ዲስኮች። እነዚህ ዲስኮች የጀርባ አጥንትን ባለበት ደግፈው ይይዛሉ። ሰውነት ከባድ ሃይል ሲያስተናግድ ሃይሉን የሚያምቁ ክፍሎች ናቸው።
ዲስክ ጠንካራ ሽፋን ያለው ሲሆን በውስጡ ግን ለስላሳ የሆነ ፈሳሽ ነው። የዲስክ መንሸራተት የሚባለው በዲስክ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ቀዳዳ ምክንያት የሚፈጠር የውስጥ ፈሳሽ መውጣት ነው። ይህ ወፍራም ፈሳሽ ነርቮችን የሚረብሽ ንጥረ ነገር በውስጡ የያዘ ነው። ይህ መረበሽ ከፍተኛ ህመም ሊፈጥር ይችላል።
የዲስክ መንሸራተት ዋነኛ መንስኤ ከግዜ ጋር የሚፈጠር የጀርባ እንቅስቃሴ ውጤት ነው። ዲስክ ከእድሜ ጋር ውሃማ ይዘቱን ያጣል። ይህ የፈሳሽ መቀነስ በዲስክ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል።
የዲስክ መንሸራተት መቼ እንደተፈጠረ ማወቅ ያስቸግራል ግን ብዙ ግዜ ቁርጭምጭሚታችንን ሳናጥፍ ከባድ እቃ ለማንሳት ስንሞክር ወይም ከባድ እቃ ይዘን ከጀርባችን ስንታጠፍ ነው።
ተጋላጭነት
የዲስክ መንሸራተት በየትኛውም እድሜ ሊከሰት የሚችል ህመም ነው። ግን ብዙ ግዜ የሚፈጠረው እድሜአቸው በ20ዎቹ ወይም በ30ዎቹ ውስጥ ያሉ ሰዎች ላይ ነው።
የጤና ችግሮች
በጣም ያልተለመደ ቢሆንም በዲስክ መንሸራተት ምክንያት ከዳሌ በታች ያለው የነርቭ ክምችት ሊጨማደድ ይችላል። ይህ ሲሆን በዘላቂነት የሚቆይ የድካም ስሜት፣ የሽንት እና ሰገራ መቆጣጠር ብቃት መዳከም እና ስንፈተ-ወሲብ ይፈጠራል።
የሚከተሉት ስሜቶች ከተፈጠሩ ዶክተር ያማክሩ፦
የሰገራ እና ሽንት መቆጣጠር ብቃት መዳከም
ኑሮአችንን በሚረብሽ ደረጃ የድካም ስሜት ከተሰማን
በውስጥ ታፋ እና እግር ጀርባ የሚፈጠር የመደንዘዝ ስሜት
ቅድመ-ጥንቃቄ
የሚከተሉትን መንገዶች በመከተል እራሳችንን ከዲስክ መንሸራተት እንጠብቃለን
ከፍተኛ የሰውነት ክብደት እንዳይኖረዎ ተጠንቀቁ
ክብደት ሲያነሱ የሰውነት አቋምን ማስተካከል
የዲስክ መንሸራተት ምልክቶች ካዩ በቂ እረፍት መውሰድ እና ተገቢውን ህክምና ማከናወን
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com