ሄፓታይተስ ቫይረስ እና የጉበት በሽታ Hepatatis Virus Infection
Author: admin
Date: 2021-08-27
ሄፓታይተስ ቫይረስ እና የጉበት በሽታ Hepatatis Virus Infection
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ጉበት ከአንጎል ቀጥሎ ስራ ብዙ የሆነ የአካል ክፍላችን ሲሆን ኬሚካላዊ ሂደቶች የሚከናወኑበት በጣም አስፈላጊው የሰውነታችን ክፍል ነው::
የጉበት በሽታ በተለምዶው የወፍ በሽታ በመባል ይታወቃል::
የአልኮል መጠጥ፣ መጠናቸው የማይታወቁ የባህል መድሃኒቶች፣የጉበት ቫይረስ ከብዙዎቹ የጉበት በሽታ ምክንያቶች ዋነኞቹ ናቸው።
በዛሬው ትምህርታችን ስለ ጉበት ቫይረስ በሽታ በሰፊው የምንመለከት ይሆናል::
የሄፓታይተስ ቫይረስ በዓይነት ብዙ ቢሆኑም በቀዳሚነት አደጋ የሚያደርሱት አምስቱ A,B,C,D እና E የሚባሉት ናቸው::
በዚህም ምክንያት 325 ሚልዮን የሚሆነው የምድራችን ህዝብ በሄፓታይተስ ቫይረስ ይኖራል።
ስንት አይነት የጉበት ቫይረስ በሽታ አይነቶች አሉ?
-ሁለት ሲሆን ጊዜያዊ(Acute) እና ዘላቂ(Chronic)ተብለው ይከፈላሉ::
በተወሰኑት ላይ ደግሞ የማይመለስ/የማይስተካከል እና የጉበት ካንሰር በማምጣት ለሞት ይድራጋሉ::
ጊዜያዊ(Acute) የጉበት ቫይረስ በሽታ
ምልክቶች?
-የሁሉም የጉበት ቫይረሶች ምልክት ተመሳሳይ ሲሆን ማቅለሽለሽ ፣ትኩሳት፣ድካም ድካም ማለትና#የአይን እና የሰውነት ቆዳ ቢጫ መሆን/በተለምዶው የወፍ በሽታ የምንለው ነው።
ጊዜያዊ(Acute) የጉበት ቫይረስ በሽታ ምን ያህል ጊዜ ይቆያል?
-ከ ሁለት እስከ አራት ሳምንት ባለው ጊዜው ውስጥ በራሱ ይድናል።
ስር ሰደድ እና አሳሳቢዎቹ የቫይረስ አይነቶች የትኞቹ ናቸው?
-ሄፓታይተስ B እና C
ሄፓታይተስ ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶቹ ምንድናቸው?
-ሄፓታይተስ A እና E ቫይረስ ንፅህና ባለመጠበቅ( በአመጋገብ /የምግብ ውሃ )የሚተላለፍ ሲሆን በብዛትም ድሃ ተብለው በሚጠሩ ሃገራት በሽታው ይበዛል::
-ሄፓታይተስ B ቫይረስ በደም ንክኪ፥በግብረስጋ ግንኙነት ፥በእርግዝና ወቅት ከ እናት ወደ ልጅ ሊተላለፍ ይችላል::
ባንፃሩ ደግሞ ሄፓታይተስ C ቫይረስ በደም ንክኪ ይተላለፋል::
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com