ሉፕ በማህጸን የሚቀመጥ የእርግዝና መከላከያ
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ይህ መከላከያ በT ቅርፅ የተሰራ በማህፀን ዉስጥ የሚቀመጥ ፕላስቲክ ሲሆን እርግዝናን በመከላከል አቅሙ እስከ 99 ፐርሰንት ነው:: ይህ ደግሞ አሉ ከተባሉ የአርግዝና መከላከያ ዜዴዎች ዉስጥ አስተማማኙ ያደርገዋል:: ሉፕ በጤና ባለሙያዎች በማህፀንዎ ዉስጥ የሚቀመጥ/የሚገባ የወሊድ መከላከያ ዘዴ ነዉ፡፡
እንደ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች በየቀኑ መዉሰድ ስለማይኖርብንና አንዴ ማህፀን ዉስጥ ከተቀመጠ ከ 3 አስከ 12 ዓመት አርግዝናን መከላከል ስለሚችል በየቀኑ ማስታወስ አይጠበቅብንም፡፡ ሉፕ በሁለት አይነት መልኩ ይገኛሉ፡፡
ኮፐር ያለበት ሉፕና
ሌቮኖርጄስትሮል ሆርሞን ያለበት ሉፕ ናቸዉ፡፡
ሁለቱም የሉፕ አይነቶች ማለትም ከመዳብ (copper) የተሰራና አና ከሆርሞን (ሌቮኖርጄስትሮል ሆርሞን) የተሰራው ሉፕ የወንድ የዘር ፍሬ ከሴቷ የዘር ፍሬ ጋር አንዳይገናኝ በማድረግ ነው እርግዝና አንዳይፈጠር የሚያደርጉት፣ እርግዝናን ከመከላከል ባለፈ ከሆርሞን የተሰራው IUD በወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰተዉን ህመም ይቀንሳል::
ለመጀመሪያ ጊዜ ሉፕ ማህፀን ውስጥ ሲቀመጥ በአንዳንድ ሴቶች ላይ የተወሰኑ የህመም ምልክቶች ሊያስከትሉ ይችላሉ እነዚህም፡-
ሉፕ በማህፀን ዉስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ሲገባ ሊያም ይችላል
ቁርጠትና የወገብ ህመም ሊያስከትል ይችላል
ጊዜዉን ያልጠበቀ የወር አበባ መምጣት
የወር አበባ ህመም መባባስ
እነዚህ ህመሞች ግን ከ 3-6 ወር ባለው ጊዜ ዉስጥ ስለሚጠፉ ብዙም ሊያሳስቡ አይገባም
ሉፕን መጠቀም የሌለባቸው እነማናቸው?
በአባላዘር በሽታዎች ከተያዙ
በእርግዝና ጊዜ
የማህፀን ካንሰር ካለ
ለኮፐር አለርጂ ከሆኑ
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com