የጡት ካንሰር ህመም መንስኤዎች
Author: admin
Date: 2021-08-25
የጡት ካንሰር ህመም መንስኤዎች
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ጡት ካንሰር በዓለማችን በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአብዛኛው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ የሚከሰት ቢሆንም በወጣት ሴቶች ላይም የመከሰት እድል አለው፡፡
የጡት ካንሰር መነሻ፡፡
1. በዘር
ይህ የካንሰር አይነት በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው ሲሆን በካንስር ህመሙ የተጠቃው የቤተሰብ አባል እናት ፣ እህት ወይንም ሴት አያት ከሆኑ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
2 ከዚህ ቀደም የጡት ካንሰር ህመም የነበረባቸው
3 ልጅ ያልወለዱ ሴቶች ወይም የመጀመሪያ ልጃቸውን እድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ከሆኑ በኋላ የወለዱ ሴቶች
4. ጡት ያለማጥባት
5. ደረታቸው ለብዙ ግዜ ለጨረር የተጋለጡ ሴቶች
6. ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያላቸውን መጠጦች ማዘውተር
7 ሲጋራ ማጨስ
የጡት ካንሰር ህመም ምልክቶች
1. በጡት ላይ እና በጡት አካባቢ የሚወጣ እባጭ
አብዘኛውን ግዜ የጡት ካንሰር ህመም ምልክት የሚሆነው ህመም የለሽ የሆነ እባጭ ነው፡፡
ይህ እባጭ አብዛኛውን ግዜ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የካንሰር አይነት ላይሆን ይችላል፡፡ነገር ግን ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡
2. የጡት መጠን እና ቅርጽ መለያየት
አንዱን ጡት ከሌላኛው ጋር በማነጻጸር የቅርጽ እና የመጠን ልዩነት ካስተዋሉ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡
3. በተወሰነ የጡት ቆዳ ላይ የመጠንከር ስሜት መከሰት
4.የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ
ይህ አይነት የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ከልጅነት (ቀድሞ የነበረ) ወይም ተፈጥሮአዊ የሆነውን የጡት ጫፍ መገልበጥ አያካትትም
5. የህመም ስሜት
አልፎ አልፎ በጡት አካባቢ የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል ፡፡ ነገር ግን የጡት አካባቢ ህመም በአብዛኛው የካንሰር ህመም ቀዳሚ መገለጫ ወይም ምልክት ላይሆን ይችላል፡፡
የጡት ካንሰር ህመም የሚሰራጭባቸው ቦታዎችን የሚከተል የህመም ምልክት ሊኖረው ይችላል፡፡
ቀድሞ የሚሰራጨው ወደ ብብታችን ስር በሚገኘው(Lymph node ) በተላበው አካባቢ ሲሆን ይህም የብብት ስር እብጠትን ሊስከትል ይችላል፡፡
የጡት ካንስር ቅድሚያ ካልተደረሰበት እና ህክምና ካላገኘ ወደ ጉበታችን እንዲሁም ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨት እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል የህመም አይነት ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም እየተበራከተ ያለ የህመም አይት ነው፡፡
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ማናኛውም አይነት የህመሙ ምልክቶች የታዩት ሠው ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በቶሎ መፍትሄ ማግኘት ይኖርበታል፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com