ላሽ (Alopecia Areata)
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ላሽ በሁለም የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች ላይ ሊከሰት የሚችል የጸጉር መመለጥ በሽታ ሲሆን፤ ይህ በሽታ በየትኛዉም የሰዉነት ክፍሎች የሚገኝ ጸጉር ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ብዙ ጊዜ ግን የራስ ቅል ጸጉርን ያጠቃል፡፡
የሚታወቁ የላሽ በሽታ ባህሪያት
• በሽታዉ በተለያየ የክብደት ደረጃ ይከሰታል፤ ከአነስተኛ የራስ ቅል ፀጉር መመለጥ እስከ ሙሉ የራስ ቅል ፀጉር መመለጥ (Alopecia Totalis) ከዚያም በከፋ መልኩ በሁሉም የሰዉነት ክፍሎች የሚገኝ ጸጉር መመለጥ (Alopecia Universalis) ፡፡
• ምን ያህለ ፀጉር እንደሚመለጥ መተንበይ አይቻልም
• በአብዛኛዉ ጊዜ በጥቂት ወራት አንዳንዴም በአመታት ጊዜ ዉስጥ ፀጉር እንደገና ሊበቅል ይችላል፤ ነገር ግን ዳግም የመብቀል እድል በተከሰተዉ ምልጠት መጠን ይወሰናል፤ መጠኑ አነስተኛ የሆነ ላሽ በአንድ አመት ዉስጥ ሙሉ ለሙሉ የመብቀል እድል ከፍተኛ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆን የፀጉር መመለጥ መልሶ የመብቀል እድሉ አናሳ ነዉ፡፡
• ዳግም የሚበቅለዉ ፀጉር ነጭ ሊሆን ይችላል፡፡
• ላሽ በአንድ ሰዉ መከሰት ከጀመረ ብዙ ጊዜ ሊመላለስ ይችላል፡፡
የበሽታዉ መንስኤ ምንድን ነዉ?
• በተፈጥሮ የተለያዩ በሽታዎችን የሚከላከል የሰዉነት በሽታ መከላከያ ስርዓት ሴሎች ፀጉርን በሚያጠቃበት ጊዜ ይከሰታል ተብሎ ቢታመንም እንዴት የሚለዉ መንገድ ግን አይታወቅም፡፡
• ላሽ እንደ ሥኳር በሽታ፤ ለምጥ፤እንቅርት ጋር መጠነኛ ተያያዥነት አለዉ
• ከምግብ፤ ቫይታሚን ወዘተ ጋር ምንም አይገናኝም
• እስከ 20 የሚደርሱ ሰዎች ተመሳሳይ ችግር በቤተሰባቸዉ (በዘር) ሊታይ ይከሰታል

የበሽታዉ ምልክቶች ምንድን ናቸዉ?
------------------------
• መጠነኛ የመወጋጋት ስሜት
• ምልጠቱ በተለያዩ ዘዴዎች መሸፈን ካልተቻለ የመሸማቀቅ (የመጨነቅ) ስሜት ይፈጥራል
• የአይን ሽፋሽፍት ከተመለጠ የአይን ቁስለት ሊከተል ይችላል በተለይ በደረቅና ንፋሳማ የአየር ሁኔታ
• በላሽ የሚመጣ ምልጠት ልሙጥ ና ምንም አይነት የቁስለትም ሆነ የቆዳ መቆጣት ምልክት አይኖርም
• ዳግም መብቀል የሚጀምረዉ ከመሐል ሆኖ ፀጉሩም ቀጠን እና ነጣ ያለ ይሆናል፡፡
• አንዳንድ ሰዎች ላይ የጥፍር መሰርጎድ ይታያል
ላሽ በህክምና (ያለህክምና) ይፈወሳል?
• ላሽ ሙሉ በሙሉ ፈዉስ የለዉም፤ መጠነኛ ላሽ ከደረሸቸዉ 5 ሰዎች ዉስጥ 4ቱ በአንድ አመት ጊዜ ዉስጥ ያለምንም ህክምና ፀጉራቸዉ ሙሉ በሙሉ ሊበቅል ይችላል፡፡ ነገር ግን ከመነሻዉ ሰፋ ያለ የፀጉር መመለጥ ያጋጠማቸዉ ሰዎች ዳግም የመብቀል እድል ሰፊ አይደለም፡፡
ለላሽ የሚሰጡ ህክምናዎች?
• ወንዶች ፀጉራቸዉ እስኪበቅል ድረስ ቀሪዉን ፀጉር መላጨት ጥሩ ስሜት ይፈጥራል፤ የራስ ቅል ቆዳ ለፀሃይ ብርሃን እንዳይጎዳ መሸፈን አስፈሊጊ ነዉ
• ሴቶች ፀጉራቸዉ እስኪበቅል በዊግ መሸፈን ምንም ጉዳት የለዉም፤ የመብቀልን ሂደት አያዉክም፤ በተጨማሪ በጥንቃቄ ዊግ መቀጠል ይቻላል
• አርተፊሻል የአይን ሽፋሽፍት፤ ቅንድብ፤ እርሳስ፤ ኩል የመሳሰለትን በጊዜያዊነት መጠቀም ይቻላል
• ዳግም የሚበቅለዉ ፀጉር ነጭ በሚሆንበት እና ለረጅም ጊዜ ቀለሙ ሳይስተካከል ከቆየ፤ ይህም የሚረብሸን ከሆነ ጊዜያዊ የፀጉር ቀለም መጠቀም ይቻላል፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com