#የማህጸን እጢ (uterine fibroids)
Author: admin
Date: 2021-08-18
#የማህጸን እጢ (uterine fibroids)
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
የማህጸን እጢዎች ምንድን ናቸዉ?
የማህጸን እጢዎች ድንች መሰል ቅርጽ፣ ይዘትና ጥንካሬ ያላቸው ከማህጸን ጡንቻ የሚነሱና የሚያድጉ እባጮች ናቸው። ማህጸን ስንል ጽንስ የሚቀመጥበት የሴት የላይኛው የመራቢያ አካል ማለታችን ነው፡፡
የማህጸን እጢዎች ተራ እባጮች እንጂ ካንሰር ወይም የካንሰር ባህሪ የተላበሱ አለመሆናቸው መገንዘብ ተገቢ ነው።
የማህጸን እጢዎች የህመም ምልክቶች ምንድን ናቸዉ?
አንዲት ሴት የማህጸን እጢ ቢኖርባትም ምንም አይነት የህመም ምልክት ላይታይባት ይችላል ። ይሁንና የማህጸን እጢዎች ያላቸው ሴቶች ከስር የተዘረዘሩት ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላል።
- የወር አበባ መብዛት
- የሆው ህመም ፣ መጫን ፣ መንፋት
- ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት
- የሆድ ድርቀት
- መጸነስ አለመቻል
የማህጸን እጢዎች ህክምናቸው ምንድን ነው?
ለማህጸን እጢዎች የሚሆኑ የተለያዩ የህክምና አማራጮች አሉ። እያንዳንዳቸው የህክምና አማራጮች የራሳቸው የሆኑ ጥቅሞችና ጉዳቶች ይኖራቸዋል። ይሁንና አንዲት ሴት የማህጸን እጢዎች ስለተገኙባት የግድ ህክምና ያስፈልጋታል ማለት አይደለም። የህክምናው አስፈላጊነት የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ ነው። ለምሳሌ
-የህመም ምልክቶች መኖር
- እድሜ (ያረጡ ሴቶች ላይ የእጢው መጠን ስለሚቀንስና የህመም ሰሜቶች ስሉሚጠፉ)
- የመጸነስ ፍላጎት
- የወር አበባ ከመብዛቱ የመጣ የደም ማነስ መኖር
- የማህጸን እጢዎቹ መጠን ፣ ብዛትና የተቀመጡበት ቦታ ወዘተ ናቸው።
ዋናዋናዎቹ የህክምና አማራጮች የሚከተሉት ናቸዉ
. የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ መድኃኒቶች
ይህ አማራጭ የወር አበባ ለሚበዛባቸው ጊዜያዊ መፍትሔ ሲሆን የማህጸን እጢዎች ቁጥርና መጠን በመቀነስ ረገድ የጎላ ተጽዕኖ የለውም ።
. በቀዶ ህክምና የማህጸን እጢዎችማውጣት (myomectomy)
ይህ አማራጭ በቀዶ ህክምና እጢዎቹን ብቻ ለይቶ ማውጣት ሲሆን ወደፊት ልጅ መውለድ ለሚፈልጉ ጥሩ አማራጭ ነው። ችግሩ ከተወሰኑ አመታት በኋላ እጢው ሊተካ መቻሉና ዘላቂ መፍትሔ አለመሆኑ ነው።
. በቀዶ ህክምና ማህጸን(ከነእጢዎቹ) ማውጣት (hysterectomy)
ይህ ህክምና ማህጸን አብሮ ስለሚወጣ የበሽታው ፍቱን መፍትሔ ነው። ችግሩ ልጅ መውለድ ለሚፈልጉ ጥሩ አማራጭ አለመሆኑ ነው።
በሃገራችን ለግዜው ጥቅም ላይ ባይውሉም ሌሎች የህክምና አማራጮችም አሉ። ለምሳሌ
. Endometrial ablation
. Uterine artery embolization
. Uterine fibroid embolization
ለማጠቃለል አንዲት ሴት የማህጸን እጢዎች ከተገኙባትና ህክምና አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ፤ ከሃኪም ጋር በመመካከር ከተጠቀሱት አማራጮች መምረጥ ይኖባታል።
. ልጅ የመውለድ እቅድ ያላት ሴት በመድሃኒት ምልክቶችን መቆጣጠር ወይም እጢዎችን ብቻ በቀዶ ጥገና ማውጣት የተሻለ አማራጭ ነው።
ልጅ የመወለድ እቅድ የሌላት ሴት ሁሉንም አማራጮች መጠቀም ትችላለች ።
. እድሜዋ የገፋና ያረጠች ሴት ከክትትል የዘለለ ህክምና ላያስፈልጋት ይችላል ።
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com