#ብሮንካይትን በቀላሉ ለማከም
Author: admin
Date: 2021-08-12
#ብሮንካይትን በቀላሉ ለማከም
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ብሮንካይት ከመተንፈሻ አካል ጋር ተያይዞ የሚከሰት የህመም አይነት ነው። በአፍንጫችን እና በሳንባችን መካከል ያለው የአየር ማስተላለፊያ ቱቦ በባክቴሪያ፣ ወይም በአይን በማይታዩ ትናንሽ ተህዋሲያን አማካኝነት፥ የመቆጣት፣ የመቁሰል እና የእብጠት ምልክቶችን ሲያሳይ የሚከሰት ነው። የህመሙ ምልክቶችም ማሳል፣ የመተንፈስ ችግር፣ ልባችን ላይ የህመም ስሜት መሰማት፣ የአፍንጫ መደፈን እንዲሁም ጡንቻችን ላይ የህመም ስሜት መሰማት እና ትኩሳት ናቸው። ይህንን ህመም በቀላሉ በቤት ውስጥ በምናዘጋጃቸው መንገዶች ማከም የሚያስችሉንን ዘዴዎች እንጠቆሙዎ፦
1 ~ ዝንጅብል
በርካታ ጊዜ ጉንፋንን ለማከም የምንጠቀመው ዝንጅብል ብሮንካይትን ለማከም እንደሚረዳ ተነግሮለታል።በዝንጅብል ውስጥ ያለው የአንቲ ኢንፈላማቶሪ ንጥረ ነገር እና በሽታን የመከላከል አቅሙ በቀላሉ የመንፈሻ አካላት ላይ የሚከሰቱ እንደ ብሮንካይት አይነት ችግሮችን ለማከም ይረዱናል።
ለዚህም ይረዳን ዘንድ የዝንጅብል ሻይ ደጋግመን መጠጣት ይመከራል።
2 ~ ነጭ ሽንኩርት
ነጭ ሽንኩርት በውስጡ ባለው የአንቲ ባዮቲክ ንጥረ ነገር አማካኝነት ብሮንካይትን ለማከም አይነተኛ ነው ይባልለታል።
ሶስት ፍሬ ነጭ ሽንኩርት ወስደን በደንብ ከፈጨነው በኋላ ወተት ውስጥ በመጨመር አንድ ላይ ደባልቀን ማፍላት፥ ከዚያ በኋላ ከመተኛታችን በፊት ሁሌም ማታ ማታ መጠጣት ይመከራል።
3 ~ እርድ
እርድ በውስጡ በያዘው የአንቲ ኢንፍላማቶሪ ንጥረ ነገር አማካኝነት ብሮንካይትን ለማከም ያስችለናል ተብሏል።ለዚህም ይረዳን ዘንድ አንድ የሻይ ማንኪያ የእርድ ዱቄት በአንድ ብርጭቆ ወተት ውስጥ በመጨመር አንድ ላይ ማፍላት።
ይህንንም በባዶ ሆዳችን በቀን ውስጥ ሁለት ጊዜ ወይም ሶስት ጊዜ ደጋግመን በመጠጣት ብሮንካይትን ማከም እንችላለን።
4 ~ ማር
ማር በተፈጥሮ ከመተንፈሻ አካላት ጋር ተያይዞ የሚመጡ በሽታዎችን ለማከም ያስችለናል። እንዲሁም ማር በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገሮች አማካኝነት የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም ከፍ እንዲል ያደርግልናል። ማርን በመጠቀም ብሮንካይተን ለማከም ይረዳን ዘንድም ሁሌም በምንጠጣው ሻይ ውስጥ አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ጨምሮ መጠጣት ይመከራል። እንዲሁም ለብ ባለ እና ከሎሚ ጋር በተደባለቀ ውሃ ውስጥ ማር ጨምረን መጠጣትም ብሮንካይን ለማከም አይነተኛ ነው ተብሏል።
የብሮንካይት ህመም በሚያጋጥመን ጊዜ ሰውነታችን ከወትሮው በተለየ በቂ ውሃ እንዲያገኝ ማድረግ ይጠበቅብናል።
ስለዚህም በቀን ውስጥ ቢያንስ ከ8 እስክ 10 ብርጭቆ መጠጣት እንደሚኖርብን ይመከራል። በተለይ ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃ ከግማሽ ሎሚ እና ማር ጋር የተደባለቀ አንድ ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ይኖርብናል።
በተጨማሪም ከጨው ጋር በተደባለቀ ውሃ ሁሌም ጠዋት ጠዋት አፋችንን እና ጉሮሮዋችንን መጉመጥመጥ ብሮንካይትን ለማከም ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ተብሎለታል።
ነገር ግን እነዚህን እየተጠቀምን የህመሙ ስሜቶች እየባሰብን ከሄ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ መታከም ይኖርብናል።
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com