#ቀዝቃዛ ውሃ ወይስ ሞቃታማ ውሃ__ለጤናዎ ጎጂ የትኛዉ ነው?
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ጤናማ ሆኖ ለመቆየት በቂ ውሃ መጠጣት አስፈላጊ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን:: ይሁን እንጂ ውሃን በተገቢው መጠን እና በትክክለኛው የሙቀት መጠን መጠጣት ለጤና አስፈላጊ መሆኑን ያዉቃሉ?
በተለይም ጠዋት ላይ ለብ ያለ ማለትም ፍሪጅ ውስጥ ያልገባ ውሃን በመደበኛነት መጠቀም ከጀመሩ:
1.ክብደት መቀነስ ይረዳዎታል: ጠዋት ጠዋት አንድ ብርጭቆ ሞቃት ውሃን ማጠጣት የሰውነት ሙቀት እና የሜታቦሊክ ፍጥነት ይጨምራል:: ይህም በሰዉነታችን ውስጥ የተጠራቀመ ስብ እንዲሰባበር በማድረግ የሰዉነት ክብደት መቀነስን ያስከትላል::የሎሚ ጭማቂ በሞቀ ውሃ ላይ በመጨመር መጠጣት በሎሚ ጭማቂ ውስጥ በሚገኘው ፔክቲን ፋይበር ምክንያት የምግብ ፍላጎቶችን ይቆጣጠራል::ይህም የክብደት መቀነስ ሂደቱን የበለጠ ያፋጥነዋል.
2. ጤናማ የምግብ መፈጨት እንዲኖር ያደርጋል:: በጠዋት ሙቅ ውሃን መጠጣት የምግብ መፈጨትን ያበረታታል::ሆድንና አንጀትን ያዘጋጃል::የምግብ መፍጫ ስርዓቱን እና ዕጢውን ያዘጋጃል::ምግቡን በቀላሉ ወደ ትናንሽ ቅንጣቶች ለመሰባበር ይረዳል::
3. ከእርጅና ጋር የተያያዘ የእድሜ መግፋትን ወይም ያለእድሜ ማርጀትን ያስቀራል:: በሰውነታችን ውስጥ ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች መኖሩ ለዕድሜ መግፋት ወይም ያለ እድሜ ማርጀት ዋነኛው ምክንያት ነው:: ይሁን እንጂ ለብ ያለ ውሃ በመጠጣት ቀንዎን ቢጀምሩ የቆዳ ሴሎችን ለመጠገን ሲረዳ ሰውነታችን ቆሻሻን እንዲያስወግድ ያደርጋል::
ቀዝቃዛ ውሃ ሲጠጡ ምን ይከሰታል?
በባዶ ሆድ ወይም ምግብ ከተመገቡ በኋላ ቀዝቃዛ ወይም ማቀዝቀዣ ውስጥ የቆየ ውኃ ሲጠጡ የተለያዩ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል::
ለምሳሌ:
- የሆድ ድርቀት ያስከትላል:: ከምግብዎ በፊት ወይም በኋላ ቀዝቃዛ ውሃ ሲጠጡ የተበላው ምግብ እና ዘይቱ በአንጀት ውስጥ የሽፋን ቅባት(ስብ) እንዲጠራቀም ያደርጋል::ይህ ለሆድ ድርቀት: ለሆድ መነፋት, ለሆድ ቃር እና አሲዳማነት የመሳሰሉ ሌሎች ችግሮችያጋልጣል::
- የደም ቧንቧዎችን በማጥበብ የደም ዝውውርን ያስተጓጉላል::
- በሰውነትዎ ውስጥ ከመጠን በላይ ዝልግልግ ፈሳሽ (MUCUS) ይፈጥራል:: ይህም በሽታ የመከላከል አቅምን ይቀንሳል,ይህም በተላላፊ በሽታዎች በቀላሉ እንድንያዝያዝ ያደርገናል::
ስለዚህ ቀዝቃዛ ውሃን በሚጠጡበት ጊዜ, ለጤንነትዎ ሊያመጣ የሚችለውን ጎጂ ውጤቶች አስቡ!
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com