#መግል ለያዘ ቁስል
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ለብጉንጅ፣ መግል ያዘለና የተደፈነ ቁስል፣ እና እባጮች የሚሆኑ የቤት ውስጥ መፍትኄዎች።
የተፈጥሮ መድኃኒት
እባጭ ከቆዳ በታች የሚገኝ መግል ያዘለ መመረዝ ነው። ነጭ ሽንኩርት ወይንም ቀይ ሽንኩርት ጥሩ መፍትሄዎች ናቸው። ነጭ ሽንኩርት ሃይለኛና ከባድ ነው። የበሽተኛው ቆዳው ሊቃጠል ወይም ቀለሙ ሊለወጥ ይችላል ሆኖም ግን ከቀይ ሽንኩርት የበለጠ መፍትሄ ነው። ቁስሉን በነጭ ሽንኩርት ዘይት መጀመሪያ ማጠብ የመድሃኒቱን ክብደትና ሃይለኛነቱን ይቀንሰዋል። በሁለቱም አንፃር የቀይ ሽንኩርት ቅባትን መጠቀም ቀላል ነው።
ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት ቆራርጦ ቁስሉ ላይ በመጠቅለያ መጠቅለል (ለረጅም ቀናት ይህን መደጋገም)
በነጭ ሽንኩርት ዘይት ወይንም በቀይ ሽንኩርት ቅባት ማፅዳት (የነጭ ሽንኩርት ዘይት እና የቀይ ሽንኩርት ቅባት ለማዘጋጀት የሚከተለውን ይመልከቱ)
የነጭ ሽንኩርት ዘይት አዘገጃጃት
አንድ የሾርባ ማንኪያ በትንሹ የተከተፈ ሽንኩርት ማዘጋጀት።
ነጭ ሽንኩርቱን ከ2 የሾርባ ማንኪያ የአትክልት ዘይት ጋር በብርጭቆ ውስጥ መቀላቀል።
በቀዝቃዛ ቦታ (2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሙቀት መጠን ባለበት ቦታ) ማስቀመጥ ( ለሶስት ዎራት አስቀምጦ መጠቀም ይቻላላ)።
ከቀይ ሽንኩርት የተዘጋጀ ቅባት አዘገጃጀት
30 ግራም ያክል ቀይ ሽንኩርት በደቃቁ ይክተፉና ለአንድ ቀን በጥላ ስር ማድረቅ።
የተፈጨውን ቀይ ሽንኩርት ከትልቅ ቆርቆሮ ሙሉ (375 ግራም) የአትክልት ዘይት ጋር መደባለቅ።
በውሃ ማሞቂያ ሙቀቱ ከ100 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሳይበልጥ ማሞቅ።
40 ግራም ሰም አቅልጦ (ወይም ሰም ከሌለ የሻማ ፍሣሽ) በዘይቱ ድብልቅ መጨመር።
በደንብ ካማሰሉ በሁዋላ በጥንሽ ዕቃቆች መገልበጥ እና በቀዝቃዛ ስፍራ ማስቀመጥ።
መግል የያዘ ቁስል መግሉን ካፈረጡ በኋላ በደንብ ማፅዳት እና የቱልት ስር ጨፍጭፎ እላዩ ላይ ማሰር ፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com