#የጡት ካንስር በሽታ ምንድን ነው ?
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ካንሰር ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ የህመም አይነቶች አጠቃላይ መጠሪያ ስም ነው ፡፡ በሽታው ከሌሎች በሽታዎች ተለይቶ የሚታወቀው ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ማደጉና ሴሎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመውረር በመቻሉ ነው ፡፡ የጡት ካንሰር በቅድሚያ በጡት ላይ በመከሰት በሽታው በአጭር ጊዜ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመዛመት የከፋ ችግር ሊያስከትል የሚችል በሽታ ነው፡፡
ጡት በተፈጥሮው በውስጡ ወተት ለማመንጨት የሚያስችሉ በርካታ ከረጢት መሰል ነገሮች እንዲሁም እነዚህን ከጡት ጫፍ ጋር የሚያገናኙ ቱቦዎች አሉት፡፡ እነዚህ ቱቦዎች በእርግዝና ወቅት ወተት ለማመንጨት ትልቅ ሚናን የሚጫዎቱ ናቸው ፡፡ የጡት ካንሰር በአብዛኛው ማደግ የሚጀምረው በእነዚህ ቱቦዎች ውስጥ ነው ፡፡ የጡት ካንሰር ተፈጠረ የሚባለው አንድ ጤነኛ ያለሆነ ህዋስ በሰውነት ውስጥ ተፈጥሮ ከገደብ በላይ መራባት ሲጀምር ነው ፡፡ የተራባው ህዋስም በጊዜ ሂደት ጤነኛ የነበሩ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ህበረ ህዋሳትን በማጥቃት በሽተኛ ያደርጋቸዋል ፡፡
ለጡት ካንሰር የሚጋለጡት እነማን ናቸው ?
የጡት ካንሰር በብዛት ሴቶችን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን የሚመጣበት ምክንያት ለጊዜው በውል አይታወቅም ፡፡ የሚከተሉት ሴቶች ግን የበለጠ ለበሽታው ተጋላጭ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ ፡፡
እድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ፤
በዘር ሀረግ በጡት ካንሰር የተያዘ ቤተሰብ ያላቸው ፤
ካንሰር ያለሆኑ ሌሎች የጡት በሽታዎች አጋጥሟቸው ከነበሩ ፤
የአልኳል መጠጥ የሚያበዙ ፤
የወር አበባቸውን ቀድመው /በልጅነት/ ያዩ ፤
ከ30 ዓመት በኋላ ልጅ የሚወልዱ ወይም ከነጭራሹ ያማይወልዱ ፤
ከሚገባው እድሜ በጣም ዘግይተው ያረጡ ፤
ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ ያያዘወትሩና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው ፤
በከፍተኛ ጨረር ውስጥ ያለ ምንም መከላከያ የሚሰሩ ፤
የጡት ካንሰር ምልክቶች ፡-
የጡት ካንሰር ሲጀምር ህመምም ሆነ ምልክቶች የሉትም ፡፡ ምልክቶችን ማወቅ በሽታውን በወቅቱ እንድናውቀው ፣ ምርመራና ህክምና በማድረግ ህይወታችንን እንድንታደግ ይረዳል ፡፡ አብዛኞቹ የጡት እብጠቶች ካንሰር ባይሆኑ ዋናኛው የጡት ካንሰር ምልክት ግን በጡት ላይ የሚከሰት ጠጣር እብጠት ሲሆን የሚከተሉት ደግሞ ተጨማሪ ምልክቶች ናቸው ፡፡
ከጡት ጫፍ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ መውጣት ፤
የጡት ጫፍ አካባቢዎች መቅላትና ወደ ውስጥ መሰርጎድ ፤
በጡት አካባቢና በብብት ውስጥ እብጠት መከሰትና ሙቀት ያለው መሆን ፤
የጡት ቆዳ መሸብሸብ / ወደ ውስጥ መግባት ወይም እንደ ብርቱካን ልጣጭም ዓይን ማውጣት/
ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊወን ህክምናና ምርመራ ማድረግ እንደሚገባ የጤና ባለሙያዎች ይመክራሉ ፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com