የጡት ፈሳሽ ህመም ከወተት ውጪ የሆነ ከጡት ሚወጣ ፈሳሽ!
Author: admin
Date: 2021-07-22
የጡት ፈሳሽ ህመም
ከወተት ውጪ የሆነ ከጡት ሚወጣ ፈሳሽ!
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
በቅንነት ሼር ያድርጉልን
ከጡት ጫፍ የሚወጣ ፈሳሽ እድሜዋ ለአቅመ ሄዋን የደረሰች ሴት ላይ ነፍሰጡር ሳትሆን ወይንም ሳታጠባ ባለችበት ወቅት ሊሰተዋል ይችላል፡፡
ሁሉም ከጡት የሚወጣ ፈሳሽ ችግር ባይሆንም እንደሚወጣው የጡት ፈሳሽ ቀለምና የሚታዩ ምልክቶች አንጻር ሊለያይ ይችላል፡፡
የጡት ፈሳሽ አይነታቸው እና መምጫ ምክንያታቸው
ነጣ ያለ፣ ደመን ያለ፣ ቢጫ ወይም መግል የመሰለ ይዘት ያለው፡- የጡት /የጡት ጫፍ ኢንፌክሽን
አረንጓዴነት ይዘት ሲኖረው ፡- ውሃ የቋጠረ እባጭ ( cyst)
ንጹህ ያልተበረዘ፡- የጡት ካንሰር በተለይ ከአንድ ጡት የሚወጣ ከሆነ
ደም የቀላቀለ፡- ካንሰር ያልሆኑ እባጮች ካሉ ወይም የጡት ካንሰር ካለ
ተያይዘው የሚስተዋሉ ምልክቶች
የጡት ህመም /መደደር
ጡት ላይ ወይም የጡት ጫፍ አካባቢ እብጠት
የጡት ጫፍ ላይ የሚስተዋል ለውጥ( ወደውስት መስመጥ፣ማሳከክ፣መላላት፣የቀለም ለውጥ…)
የጡት መቅላት
የጡት መጠን ለውጥ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ
ትኩሳት
የወር አበባ መዛባት
ማጥወልወል/ማስመለስ
የድካም ስሜት
መቼ ባለሙያ ላማክር ?
ጡት ላይ እባጭ ካለ
የጡት ጫፍ (nipple)ለውጥ ካለ
ህመም ካስከተለቦት
ደም የቀላቀለ ከሆነ
እና ፈሳሹ ለረጅም ጊዜ ከቀጠለ/ካላቆመ
የሚሰሩ #ምርመራዎች
የጡት አልትራ ሳውንድ
ማሞ ግራፊ
እንዲሁም ሰምፕል ወስዶ የሚሰራ ምርመራ (biopsy)
• መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
• https://www.facebook.com
• telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com