የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
Author: admin
Date: 2021-07-19
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
የሽንት ቧንቧ ማለት ኩላሊትን፣ የሽንት ፊኛን እና በመሃል የሚገኙትን አስተላላፊ ቱቦዎችን ይጨምራል። አብዛኛው ኢንፌክሽን በሽንት ፊኛ ላይ የሚከሰት ሲሆን በአፋጣኝ ካልታከመ ወደኩላሊት በመሰራጨት ከባድ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እንዴት ይከሰታል?
ጀርሞች በውጪኛው የሽንት ቧንቧ በኩል ወደፊኛ በመግባት ኢንፌክሽን እንዲከሰት ያደርጋሉ። እነዚህ ጀርሞች የሚገኙት በትልቁ አንጀት ውስጥ ሲሆን በሰገራ በኩል ወደውጪ ይወጣሉ። ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ የሆኑት ሴቶች ሲሆኑ ይህም የሆነበት ምክንያት የሴቶች ሽንት ማስተላለፊያ ቱቦ ከወንዶች ሲነፃፀር አጭር በመሆኑ ነው። በዚህም ምክኒያት የሽንት ፊኛ በቅርብ ይገኛል ማለት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ የጀርሞችን ወደፊኛ መጓዝ ያፋጥነዋል።
ፈሳሽ በበቂ ሁኔታ የማይወስዱ፣ የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች፣ እንዲሁም ነፍሰ-ጡር የሆኑ ሴቶች የመያዝ ታጋላጭነታቸውን ይጨምራል። በተመሳሳይም የኩላሊት ጠጠር መኖር እንዲሁም የፕሮስቴት ችግር መኖር ተጋላጭነትን ይጨምራል። በሽታው በተደጋጋሚ የመከሰት ባህር ይታይበታል።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶቹ ምንድናቸው?
በመሽናት ጊዜ የማቃጠል ወይም የህመም ስሜት
በተደጋጋሚ የመሽናት ፍላጎት ፣ ሲወጣ ግን መጠኑ ትንሽ መሆን
የሆድ መነፋት ስሜት
የሽንት መልክ መቀየር ወይም ሽታ ማምጣት
የጀርባ ህመም
ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት
ማቅለሽለሽና ትውከት
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መቼ ሊያሰጋኝ ይችላል?
በአፋጣኝ ወደ ሐኪም መሄድ የሚሹት ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡
ዕድሜ ከ 65 በላይ ከሆነ
ኤች አይ ቪ ቫይረስ በደሞ ውስጥ የሚገኝ ከሆነ
የስኳር ወይም ሌላ የኩላሊት ችግር ካለብዎት
ነፍሰጡር ከሆንሽ
በእነዚህ ጊዜያት ህክምና ካልተገኘ አስከፊ ችግሮች ሊከተሉ ይችላሉ።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ህክምናው ምንድነው?
የሽንት ምርመራ ከተደረገ በኋላና ኢንፌክሽን መሆኑ ከተረጋገጠ ፀረ-ተህዋስ (antibiotics) መድሀኒት ይታዘዛል። ከመድሀኒቱ በተጨማሪ ብዙ ውሀ መጠጣትና ቶሎ ቶሎ መሽናት ይጠቅማል።
መድሀኒቱ እየተወሰደም የመሻል ምልክቶች ቢታዩም የታዘዘው መድሀኒት እስከሚያልቅ ድረስ ማቋረጥ አያስፈልግም። መድሃኒቱ በትክክል ካልተወሰደ ባክቲሪያዎቹ መድሀኒቱን ለመልመድ ጊዜ ስለሚያገኙ ለህክምና አስቸጋሪ ሁኔታ ይፈጥራል። በተደጋጋሚ መከሰትም ይጀምራል።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እንዴት መከላከል እችላለሁ?
በሽታው እንዳይከሰት፤ ብዙ ውሀ በመጠጣት እና ሽንት ሲመጣ ሳይዙ ቶሎ በመሽናት መከላከል ይቻላል።
• መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
• https://www.facebook.com
• telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com