የስጋ ደዌ በሽታ
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
የስጋ ደዌ በሽታ ማይኮባክቴሪየም ሌፕሬ በተሰኘ ረቂቅ ተህዋስ ወይም ጀርም አማካኝነት የሚመጣ በሽታ ነው፡፡
የሥጋ ደዌ በሽታ ማንን ያጠቃል?
የሥጋ ደዌ በሽታ በሁሉም የኑሮ ደረጃና በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ
ወንዶችና ሴቶችን እኩል ያጠቃል፡፡ ይሁን እንጂ በአብዛኛው በይበልጥ
የሚጠቁት በ15 እና በ 45 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ወይም በአምራች የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡
ድህነት የተመጣነ ምግብ ዕጦትና ለጤና ተስማሚ ባልሆነ ቤት ውስጥ ተፋፍጐ
መኖር ለሥጋ ደዌ በሽታ የሚያጋልጡ ናቸው፡፡
የሥጋ ደዌ በሽታ ምልክቶች ምንድ ናቸው?
በፊትና በጆሮ ላይ የብጉር መሰል ጉብታዎች
የነርቮች ማበጥና ሕመም
የእጅና የእግር መደንዘዝ የሥጋ ደዌ በሽታ ምልክቶች ናቸው፡፡
የሥጋ ደዌ በሽታ እንዴት ይተላለፋል?
አንድ ሰው በሥጋ ደዌ በሽታ ሊጠቃ የሚችለው ሕክምና ካልጀመረ የበሽታው
ተጠቂ ከሆነ ሰው ጋር ለረጅም ጊዜ አብሮ በመኖር የቅርብ ግንኙነት ሲኖረው
ነው፡፡
ልብ ይበሉ የሥጋ ደዌ ሕመምተኛ ሕክምና ከጀመረ ወይም ታክሞ ከዳነ
በሽታውን በፍፁም ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡
፩. የሥጋ ደዌ በሽታ በዘር፣ በእርግማን የሚመጣ በሽታ አይደለም፡፡
፪. የስጋ ደዌ በሽታ ሙሉ በሙሉ በህክምና ይድናል።
የሥጋ ደዌ በሽታ መኖር እንዴት ሊረጋገጥ ይችላል?
፩. በቆዳ ላይ ነጣ ነጣ ወይም ቀላ ብለው የሚታዩ ምልክቶች በጥጥ ሲነኩ
ስሜት አልባ ከሆኑ ወይም ስሜት ከሌላቸው
፪. በዳሰሳ ምርመራ የነርቭ እብጠት መኖር ያለምንም ጥርጥር ሲረጋገጥ
፫. በሽታው እንዳለበት ከተረጋገጠ የጤና ባለሙያ በሚያዘው መሰረት
መድኀኒቱን ሳያቋርጥ ሙሉ በሙሉ ወስዶ መጨረስ አለበት፡፡
#መፍትሔ
#የወርቅ በሜዳ ስር
የወርቅ በሜዳ ስሩን ነቅሎ ሰብስቦ በንፁህ ቦታ አድርቆ በንፅና ቀጥቅጦ አልሞ በሻይ ማጥለያው ወንፊት ነፍቶ የተነፋውን ዱቄት በስኳር ማንኪያው አንድ ሦስት የሾርባ ማንኪያ ማር በመጨመር በጥብጦ ጥዋት በባዶ ሆድ መውሰድ የተወሰነ ወደታች ሊል ይችላል
መድሐኒቱን ከተጠቀሙ በኋላ እስከ ዘጠኝ ሰአት ምግብ አይብሉ ከዘጠኝ ሰአት በኋላ ተኮስ ያለ ነገር መመገብ።
ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የለውም
ይህን ድርጊት በየሳምንቱ ሁለት ቀን እያደረጉ ለተከታታይ ለሦሥት ሳምንት(6) ቀን ቢጠቀሙት በሰውነት ውስጥ ያለውን የስጋ ደዌ ፈፅሞ ይጠፋል ወይም ከስጋ ደዌ ፈፅሞ መዳን ይቻላል በሽታው በተቅማጥ መልክ ይወገዳል ።
• መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
• https://www.facebook.com
• telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com