የሚጥል በሽታ (Epilepsy)
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
በአሁን ወቅት የህክምና ጠበብት ከ30 በላይ የሚጥል በሽታ አይነቶችን ለመለየት የቻሉ ሲሆን ወደ 10 በመቶ የሚጠጉ የአለማችን ህዝቦች በህይወት ዘመናቸው ቢያንስ አንዱን አይነት የሚጥል በሽታን ያስተናግዳሉ፡፡ ከሚጥል በሽታ አይነቶች ውስጥ ከሁሉም እጅግ የታወቀው ‹‹አብሰንስ ሲዘር›› (absence seizure) የሚባለው የበሽታ አይነት ነው፡፡ ይህ አይነቱ የሚጥል በሽታ በአብዛኛው በልጆች ላይ የሚከሰት ሲሆን፤ የበሽታው ተጠቂም ጥቂት ሰከንዶች ላልበለጠ ጊዜ ንቁ ያለመሆንና የመደንዘዝ ሁኔታ ይስተዋልበታል፡፡ በአንዳንድ ልጆች ላይ በቀን ውስጥ ለበርካታ ጊዜዎች ሊከሰትም ይችላል፡፡ ምልክቶቹም አዘውትሮ ወደ አንድ አቅጣጫ እያዩ መፍዘዝና ንቁ አለመሆን፤ በተደጋጋሚ ዓይንን ማርገብገብ፤ ለነገሮች ጥብቅ (ድርቅ) ያለ አቋም እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ እንዲሁም አንዳንድ የሰውነት ክፍሎች በዝቅተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ሲሆን በተጨማሪም ለአነቃቂ ህዋስ በጭራሽ ምላሽ ላይሰጡና የታዘዙትን መስራት እንዳይችሉ ሊያደርግ ይችላል፡፡
የሚጥል በሽታ አዕምሯችን የሚሠራበትን መንገድ የሚነካ የጤና እክል ሲሆን የታማሚው ሰውነት ለአጭር ጊዜ እንዲንዘፈዘፍ ማድረጉም ሌላው መገለጫው ነው። ሰውነቱ የሚንዘፈዘፍበት ጊዜ በአብዛኛው ከአምስት ደቂቃ አይበልጥም። ሕመሙ የሚነሳውም የአእምሮአችን ህዋሳት ከትክክለኛው ስርአት በተለየና በበዛ መልኩ ሲነቃቁ የሚከሰት ሲሆን በተጨማሪም በአንጎል ሴሎች መካከል ያለው የኤሌክትሪክ ፍሰት ሲዛባ እንደሆነ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ። እንዲህ ያለው ሁኔታ የሚከሰትበት ምክንያት ግን እስካሁን ድረስ መልስ አልተገኘለትም።
የሚጥል በሽታ ያለባቸው ብዙ ሰዎች፣ በሽታው አጉል ጊዜ/ቦታ ላይ እንዳይነሳባቸው ሁልጊዜ እንደሚሰጉ ለመረዳት አያዳግትም። የሚያሳፍር ሁኔታ እንዳያጋጥማቸው ሲሉ ብዙ ሰዎች ባሉበት አካባቢ ላለመገኘት ሊመርጡ ይችላሉ። ይህ ደግሞ ከፍተኛ የስነልቦና ጫናን ያደርስባቸዋል፡፡ ለሚጥል በሽታ ከሚያጋልጡ መንስኤዎች መካከል በዘር የመተላለፍ ሁኔታ የመጀመሪያው ቢሆንም፤ ተፈጥሮአዊ የሆነ የአዕምሮ እክል፣ በልጆችና በጎልማሶች ላይ የሚደርስ የጭንቅላት አደጋ ወይም ኢንፌክሽን፣ ከፍተኛ በሆነ ትኩሳት ምክንያት የሚከሰት ድንገተኛ የሆነ ራስን መሳት እና የአንጎል ዕጢ ሌሎች ተጠቃሽ መንስኤዎች ናቸው፡፡ በአንዳንድ የበሽታው አይነቶች ላይ ሁኔታው ከመከሰቱ በፊት ራስ ምታት፣ ከፍተኛ የልብ ምት ስሜት፣ የእይታ ብዥታ ሊታዩ ይችላሉ። ይህም ከአንድ እስከ ሁለት ደቂቃ ሊቆይ ይችላል። ታማሚው ከነቃ በኋላ የሆነውን ነገር ለማወቅ እና ለማስታወስ ይሳነዋል።
በሚጥል በሽታ የተያዙ ሰዎች ከዚህ በሽታ ለመገላገል በርካታ ነገሮችን ቢያደርጉም ከየትኛውም መፍትሄ በላይ ግን የህክምና ክትትል ማድረግ ዋነኛው ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ የሚጥል በሽታ ላለበት ሰው ስሜቱን አውጥቶ እንዲገልጽ በማበረታታት፣ ጥሩ አድማጭ በመሆን እና ህመምተኛው ሕመሙ ሲነሳበት ምን እንዲደረግለት እንደሚፈልግ በመጠየቅ ድጋፍ መስጠት ይቻላል፡፡

- ባህላዊው መድሀኒት
1. የጂባራ ወተት ፣ የውሻ እና የጅብ ሀሞት በአፍንጫው ውስጥ ማሽተት፡፡
2. የግሚ ሀረግ ፣ የቀይ ግመሮ ፣እፀ መናኒ፣ የጅባራ ስር እና አርማጉሳ ቅጠላቸውን ወቅጦ በመራራ ቅል ዘፍዝፎ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በአፍንጫ ማድረግ ፡፡
• መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
• https://www.facebook.com
• telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com