የጨቅላ ህፃናት ቢጫ የመሆን በሽታ (neonatal jaundice)
Author: admin
Date: 2021-07-12
የጨቅላ ህፃናት ቢጫ የመሆን በሽታ (neonatal jaundice)
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ጨቅላ ህፃናት እንደተወለዱ ከሚያጋጥማቸው ችግሮች ዋነኛውና በብዛት የሚታየው የጨቅላ ህፃናት እንደተወለዱ
እንዲሁም በመጀመሪያው ሳምንት የአይን እንዲሁም የቆዳ ቀለም ወደቢጫነት የመቀየር በሽታ ነው፡፡ይህ በሽታ Bilirubin
የተባለ ኬሚካል በሰውነታቸው ውስጥ መጠራቀም እና መብዛት የሚያመጣው ነው፡፡ይህ ችግር ብዙ ጊዜ በጥሩ ፀሀይ
ብርሃንና በደንብ ጡት በማጥባት የሚቀንስ እንዲሁም የሚወገድ ቢሆንም መጠኑ ከባድ ከሆነ ግን በህፃናት እድገት ላይ
መጥፎ ጫና ሊያመጣ ስለሚችል የጤና ባለሙያ ማሳየት አስፈላጊ ነው፡፡
የሚከሰትበት ምክንያት
ይህን ችግር የሚያመጡ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም ጨቅላ ህፃናትን በተመለከተ ዋናዋናዎቹ ምክንያቶች
ቢሊሩቢን የተባለው ኬሚካል ከሰውነታችን በደም ህዋሳት አማካኝነት በሽንትና አይነምድር የሚወገድ ሲሆን ለማስወገድ
አዲስ የሆኑት የደም ህዋሳት እስኪለማመዱ ያለው ጥርቅም ይህን ቢጫነት ይፈጥራል፡፡
ባጠቃላይ ይህ ችግር- የተፈጥሮአዊ ለውጥ ችግር እንዲሁም- በሌላ ህመሞች ምክንያት የሚመጣ ችግር ብለን ልንከፍለው እንችላለን
የተፈጥሮአዊ ለውጥ ችግር (nonorganic causes)
ይህ የተለመደው ወይም በብዛት የሚታየው አይነት የቢጫነት አምጪ ምክንያት ከሚያመጡት ምክንያቶች ዋናዋናዎቹ
• ጡት በደንብ አለመጥባት
• የጨቅላ ህፃናት ጨጏራ ውስጥ የሚያስፈልጉ ጠቃሚ ተህዋሲያን ቁጥር ማነስ
• ከጊዜያቸው በፊት የተወለዱ ህፃናት የደም ህዋሳታቸው ኬሚካሉን ማጣራት አቅም ማጣት
• የአንዳንድ የጡት ወተት ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች በጨቅላ ህፃናት የመጀመሪያዎቹ ቀናት መፈጨት ወይም መብላላት አለመቻል፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች የተለመዱና ብዙ ጨቅላ ህፃናትን ሊያጠቁ ስለሚችሉበተለየ ቀለም(ሰማያዊ) ብርሀን ህክምና በቀላሉ ሊጠፉ የሚችሉ ናቸው፡፡
በሌሎች ህመሞች ምክንያት የሚመጣ ቢጫነት (pathologic/organic cause)
በጣም ብዙ ህመሞች የጨቅላ ህፃን ቢጫነትን ሊያመጡ ይችላሉ ለምሳሌ
• የደም ህዋሳት አፈጣጠር ችግር
• የሰውነት ኬሚካሎች (enzyme)እጥረት
• በቫይረስ/ በባክቴሪያ የሚመጡ የጨቅላ ህፃናት ኢንፌክሽን
• የእናትና የጨቅላው ህፃን የደም አይነት ልዩነት በተለይ እናት ደም አይነት O ከሆነ
• የጨቅላ ህፃናት አንጀት መቋጠር/መዘጋት
ከላይ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ያልተለመዱ ወይም በብዛት ምክንያት ባይሆኑም በእነዚህ ምክንያቶች የጨቅላ ህፃናት ቢጫነት ሊፈጠር ይችላል፡፡
የሚያመጡት ምክንያቶች
ይህ ችግር ያጋጠማቸው ጨቅላ ህፃናት ከሚታይባቸው ዋናዎቹ
• የአይናቸው ነጩ ክፍል ቢጫ ቀለም ይለውጣል
• መነጫነጭና በደንብ አለመተኛት
• መጥባት ማስቸገር ወይም ማቆም
• ንቁ አለመሆንና መተኛት
• የደማቸው Bilirubin መጠን በብዛት ከ10ሚግ/ዴሲሊትር በላይ መጨመር
• ሳይታከም ከቆየ የሰውነት ማንቀጥቀጥ የፊት አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች ስራ ማቆም
እነዚህ ምልክቶች ከታዩ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቀም መተው በደማቸው ውስጥ የሚገኘው የbilirubin መጠን መለካት ይኖርበታል፡፡
ህክምና
• በተለይ በተፈጥሮአዊ ለውጥ ችግር እንዲሁም በደም አይነት ልዩነት የሚመጣ የጨቅላ ህፃናት ቢጫነት ቶሎ ወደ ጤና ተቋም ማምጣት ከተቻለ
• በተለየ ቀለም(ሰማያዊ) ብርሀን ህክምና (photothreapy) እንዲሁም በደንብ በማጥባት መቀነስ እንዲሁም ማጥፋት ይቻላል
• ነገር ግን መጠኑ ከ25ሚግ/ዴሲሊትር በላይ ከሆነ ደምን እያጣራ የሚመልስ መሳሪያ ላይ በፍጥነት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ባጠቃላይ ለወላጆች ዋና ማወቅ የሚገባው
• ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ከታየ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም ማምጣት
• የቀለም ብርሃን ህክምና ካስፈለገው በየሁለት ሰአቱ በደንብ ማጥባት
• በትንሹም ቢሆን ቢጫነት ብቻ(ሌሎቹን ምልክቶች ሳያሳይ)ከታየ ከ5-6 ሰአት ባለው የፀሀይ ብርሀን ለ10-20ደቂቃ ማስመታት አስፈላጊ ነው፡፡
• መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
• https://www.facebook.com
• telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com