አይነሰብ ( ቡዳ ) እና አይነጥላ
Author: admin
Date: 2021-07-09
አይነሰብ ( ቡዳ ) እና አይነጥላ
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
#ቡዳ ምንድነው ?
መንፈስ ነው ወይስ ሰይጣን?
ወይስ የሰው ተፈጥሯዊ ዓይን ችግር ?
ወይስ ከብዙዎች መካከል ጥቂቶች የሚሰጣቸው የፀጋ ስጦታ እንደሚሉት ነው ?
ወይስ በልምምድ የምናዳብረው የሦስተኛ ዓይን ኃይል ነው ?፡-
በእውነት ግን ቡዳ ምንድነው ?
✿.... ስለ ቡዳ መንፈስ ሲነሳ ርኩስ መንፈስነቱን የሚያውቅና የማያውቅ በ50% ግማሽ በግማሽ ተመድበው የሚከራከሩ ብዙ ህዝቦች አሉ
ከዚህም ጋር በተያያዘ የቡዳ መንፈስ ተግባር የሚጀምረው ወይም ስራውን የሚያከናውነው በአይን በኩል እያጮለቀ እንደሆነ 100% ሙሉ በሙሉ ሁሉም ሰዎች ያምኑበታል፡፡
በመላው አለም ያሉት አይኖች በማን ቁጥጥር ውስጥ እንደሆኑ በማጥናት የሚያመሳስለንን ጸባይና ፤የጤና ፤የበሽታ ፤የአመለካከት ሁኔታ ፤ በማጥናት ማድረግ የማንፈልገውን ህይወት እያደረግን በግዳጅ ህይወት ውስጥ ተወትፈን ማየትና መዳሰስ መቅመስና መተንፈስ የሚገባንን ተነፍገን ለሌላ ሃይል እንደተያዝን ያላወቅን ሆነን ስለጉዳዩ ሲነገረን የባሰ ብሎ ግር የሚለን ብዙ ነን
ስለአይንና ስለቡዳ ሲነሳ ብዙ ጊዜ ለማዳመጥ ወይም ነገሩን ጉዳዬ ነው ብሎ ለማስተዋል የሚፈልግ ሰው ያለ አይመስለኝም ፡፡
ምክንያቱም ሁሉም ትውልድ እርሰ በእርስ በሚያነካክስና በሚያበላላ መንፈስ ስለተበላና ስለታኘከ እንዲሁም በስተእርጅና ስለተረገጠ፡፡
ለአሁን በጥቂቱ የቡዳ አይነጥላን መንፈስ ባህሪውን ልግለጥና የቡዳን ማንነት በኢትዮጵያውያን አይን እይታና በመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች እያብራራን እናያለን፡፡
ላሁን ቡዳ የአይነጥላ መንፈስ የሚሰራው በሁለት መንገድ ነው፡፡
1ኛ. እያባበለ እያረሳሳ ሳይታወቀን ከመንፈሳዊ ማንነትን ከስላሴ ልጅነት እያስወጣ አለማዊ የማድረግ ባህሪ አለው፡፡ ግን የቡዳነቱን ፀባይ እየቀላቀለ፤ የነካነውን በሙሉ እያበላሸ፤ እድለቢስ ነኝ እንድንል ያሰለጥነናል ፤በተጨማሪም አይነጥላነቱ እንዳይነቃበት ሲል ያለማመደንን ህይወት አንቀበልም ስንለው የሰጠንን ስራና እውቀት መልሶ በመንቅ ያስደነግጠናል፡፡
2. ሌላው የቡዳ አይነጥላ ልዩ መገለጫው በዙሪያችን ያሉትን ሰዎች ከትንሽ እስከ ትልቅ እንድንጠላቸውና እንዳናምናቸው በማጠራጠር የጎሪጥ ወይም "በቆሪጥ መንፈስ" ይተያያናል ሁሉ ነገራችንና ሁሉ ነገራቸው አንዳይጣጣም ይለየናል፡፡
*....በተጨማሪም መልካችንንና ንብረታችንን ልጆቻንንና ማንኛውም የኛ የሆነ ነገር ላይ በማፍጠጥ እግር በእግር እየተከታተለ የተቃራኒውን ህይወት ውጤት ያሳየናል፡፡
* በአይን ውስጥ መቀመጫውን ካደረገ መንፈስ አንዱና ዋነኛው ቡዳ ነው ...* የአይነጥላ መንፈስ በሁለት አይነት መንገድ ይገለጣል፡፡
1. የዛር አይነጥላ .....
2. ቡዳ አይነጥላ
✿..... ቀድመን እንዳነበብነው ብቻ ሳይሆን በግልጽ ተከስቶ በአይን እያጉረጠረጠ በአፍ እያሽሟጠጠ በጥርስ እያፋጨ በገሃድ የሚዋጋ የድብቅ ሚስጥሩን ጨርሶ በግልጽ የሚገድል ጦረኛ ነው
ስለዚህ መንፈስ ጻድቁ እዮብ እንዲህ ብሏል
"... ጠላቴ አይኑን አፈጠጠብኝ በቁጣው ቀደደኝ እርሱም ጠላኝ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ ..." ይላል እዩ፡-16፤9
ስለዚህኛውም መንፈስ ኢትዮጵያውያን በቂ መረጃና የጠለቀ እውቀት አላቸው እንዲያውም ስለቡዳ መንፈስ በአለም ላይ ያላቸው አመለካከት የተሳሳተ ሆኖ "...አንዴ ሶስተኛው አይን ሲባል ፤አንዴ ስድስተኛውን ስሜትና ህዋስ ፣ሲባል ኑሯል ።
እንዴት በባህላዊ ህክምና መታከም እንችላለን
የጅብራ እና የእፀ መናኒ ቅርፊት ፣ የግመሮ፣ የግዜዋ፣ የምድር እንቧይ ፣ ታሪገማ ስራቸውን የጅብ ጉበት እና የመጨላ ስር በአንድ ላይ ወቅጦ መታጠን ወይም በጅብ ሀሞት ለውሶ መያዝ፡፡
ለአይነ- ጥላ የግዜዋ ስር ፣ ጤና-አዳም ፣ የምስርች ቅጠል እና ኮረሪማ አንድ ላይ ቀቅሎ ለሁነት ቀን በማር መውሰድ ፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com