የማህፀን ጫፍ ካንሰር
• የማህፀን ጫፍ ካንሰር
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ

በአለማችን ያሉ ሴቶችን በብዛት ከሚያጠቁ የካንሰር በሽታዎች አራተኛውን ደረጃ የያዘው የማህፀን ጫፍ
ካንሰር የሚባለው የካንሰር ዓይነት ነው፡፡ ይህን በሽታ ለየት የሚያደርገው ከ80% በላይ የሚያጠቃዉ መካከለኛና
ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች የሚኖሩ ሴቶችን መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ቅድሚያ በሚሰጡ ክትባቶች እንዲሁም በግዜ
አግኝቶ ለማከም የሚረዳውን (papsmear) የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ በማድረግ መከላከል ይቻላል፡፡

• አጋላጭ መንገዶች
የማህፀን ጫፍ ካንሰር ዋናዎቹ አጋላጭ መንገዶች የሚከተሉት ናቸ፡፡
1. (HPV) ቫይረስ
በዚህ ካንሰር ከመጋለጥ ዋና ዋናዎቹ መንገዶች አንዱ ልቅ በሆነ የግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፈው ይህ ቫይረስ
ሲሆን ብዙውን ጊዜ በሽታው ምልክቶች ሳይኖሩት በሰውነት ውስጥ ኖሮ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ሊያመጣ ይችላል፡፡
ይህን ለመከላከል የሚረዳ ክትባት እድሚያቸው ከ 17 – 25 እንዲሁም ከ 25-40 ዓመት ላሉ ሴቶች መስጠት ተጀምሯል፡፡
2. ሲጋራ ማጨስ
3. የአባላዘር በሽታ የተያዙ ሴቶች (HIV) ጨምሮ
4. ለረጅም ጊዜ ማለትም ከ5 አመት በላይ በክኒን የሚወሰዱ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል የሚወስዱ
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ መንገዶች በጥቂቱ ምክንያት ሊሆኑ ቢችሉም በተለይ በHPV ቫይረስ መጠቃት ግን በሁሉም
በበለጠ ተፅእኖ የሚያመጣ መንገድ ነዉ፡፡

ምልክቶች
የማህፀን ጫፍ ካንሰር ወደ ውስጠኛው የማህፀን በር ክፍል ገብቶ በደንብ ከመዛመቱ በፊት በተያዘችው
ሴት ላይ ምንም ዓይነት ምልክቶች አያሳይም፡፡ ይህም ነው የማህፀን ጫፍ ምርመራ (papsmear) ለሁሉም
ከ 22 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ቢያንስ በዓመት አንዴ መመርመር በጣም አስፈላጊ እንደሆነ የሚነገረዉ፡፡
ከመዛመቱ በፊት ማወቅ ከተቻለ ከነጭራሹ ማጥፋት ይችላል፡፡ ይህ ሊሆን ካልቻለ ግን
1. ከወር አበባ ውጪ ከማህፀን የደም መፍሰስ
2. በግንኙነት ጊዜ ህመም ወይም መድማት መኖር
3. ሀይለኛ ሽታ ያለው የማህፀን ፈሳሽ መኖር
4. እንዲሁም የማህፀን አካባቢ ህመም እንደ ምልክት ሊታይ ይችላል፡፡

ህክምና

አንዲት ሴት የማህፀን ካንሰር መያዟ ከታወቀ በኋላ በመጀመሪያ የተዛመተበት ደረጃ መታወቅ አለበት፡፡
ይህንን በመመርኮዝ ህክምናውን መምረጥና መስጠት ይቻላል፡፡ ደረጃውም የሚወስነው ከማህፀን ጫፍ ላይ
ብቻ መሆኑን ወይም ከዛ አልፎ የሰውነት ማጣሪያ ዕጢዎች (lymphnodes) መግባቱን እንዲሁም ከዛም
አልፎ ወደ ሌሎች የሰዉኑት ክፍሎች መዛመቱን በማረጋገጥ ነው፡፡

እነዚህ ህክምናዎች የሚከተሉት ናቸው

በማህፀን ጫፍ ላይ የተወሰነ ከሆነ በቀዝቃዛ ናይትሮጅን አማካኝነት የካንሰሩን ቦታ የማጥፋት ህክምና (cryotherapy).
ከዚህ አልፎ ወደ ሁለተኛው ክፍል ከገባ የጨረር እንዲሁም የኬሞቴራፒ ህክምና ከማህፀን ጫፍ ቀዶ ጥገና ጋር
በመጨረሻም ወደሌሎች የሰውነት ክፍሎች ከተዛመተ ሙሉ የማህፀን ማውጣት ቀዶ ጥገናን ጨምሮ የጨረርና
የኬዎቴራፒ ህክምና ሊያሳፈልግ ይችላል፡፡
ባጠቃላይ ማንኛውም ሴት አሰቀድማ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ (papsmear) በማድረግ እንዲሁም
የ HPV ቫይረስ ክትባት በመውሰድ ይህንን ከ270,000 በላይ ሴቶች በአመት የሚገድለውን አደገኛ ካንሰር መካላከል ትችላለች፡፡

ከዚህ ጋር ተያያዞ ለማስጠንቀቅ የምንወደው በዚህ ከሚሞቱት ሴቶች 80% የሚሆኑት በታዳጊ አገር የሚኖሩ በመሆናቸው
የተለየ ጥንቃቄና ትኩረት እያንዳንዱ ሴት ሊሰጥ እንደሚገባና አጋላጭ መንገዶቹን በማሰወገድና መከላከያ መንገዶችም በመጠቀም
የመያዝ መጠኑን በደምብ መቀነስ እንደሚቻል ነው፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com