የስኳር ህመም እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?
Author: admin
Date: 2021-06-25
የስኳር ህመም እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
የስኳር ህመም በዓለማችን ላይ ብዙ ሰዎችን ከሚያጠቁና ተላላፊ ካልሆኑ ህመሞች የሚካተት በሽታ ነው፡፡ ሰውነታችን ኃይል ለማግኘት ሲል የተመገበውን ምግብ ወደ እያንዳንዱ ህዋስ ገብቶ ኃይል እንዲሆናቸው የሚያግዘው እንሱሊን የተሰኘ በሰውነታችን ውስጥ የሚመረትና፤ ሰውነታችን ውስጥ ከሚገኘው የስኳር መጠን ጋር አብሮ ከፍ በማለት በደም ውስጥ የስኳር መጠንን የሚቆጣጠር ሆርሞን ነው፡፡ ሆኖም ግን ኢንሱሊን በሚፈለገው መጠን መመረት /እጥረት/ አሊያም ከሰውነት ህዋሶች ጋር መናበብ ሲያቅተው የስኳር ህመም ይከሰታል፡፡
ከዚህም የተነሣ የስኳር ህመም የተጠቃ ሰው በደሙ ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ከተለመደውና ከትክክለኛው ለኃይል ሰጪነት የሚያገለግለው መጠን በጣም ከፍ ይላል፡፡
የስኳር ህመም ዓይነቶች
የመጀመሪያው አይነት የስኳር ህመም
በማንኛውም የእድሜ ክልል ሊከሰት የሚችልና በአብዛኛው በወጣትነትና ከዚያ በታች ባለ እድሜ ክልል የሚታይ ሲሆን፤ የሚከሰተውም ኢንሱሊን የሚያመርተው ቆሽት በጣም ትንሽ ወይንም ምንም ማምረት ሲያቅተው ነው፡፡ ሁልጊዜም የኢንሱሊን ሆርሞንን የመወጋት ክትትል የሚፈልግ አይነት ነው፡፡ በተጨማሪም ትክክለኛ የምግብ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ እና የመሣሠሉት ያስፈልጉታል፡፡
ሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም
ይህ አይነት ከ40 ዓመት በላይ በአብዛኛው የሚከሰትና የተለመደው የስኳር ህመም ነው፡፡ ውፍረት ለዚህኛው የስኳር አይነት በአብዛኛው የሚጋልጥ ሲሆን በአፍ የሚዋጡ መድኃኒቶችን በመውሰድ፣ ኢንሱሊን በመወጋት ወይም ሁለቱም በመጠቀም የምንቆጣጠረው ነው፡፡ በተጨማሪም ትክክለኛ የምግብ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ እና የመሣሠሉት ያስፈልጉታል፡፡
ሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም
ይህ አይነት ከ40 ዓመት በላይ በአብዛኛው የሚከሰትና የተለመደው የስኳር ህመም ነው፡፡ ውፍረት ለዚህኛው የስኳር አይነት በአብዛኛው የሚጋልጥ ሲሆን በአፍ የሚዋጡ መድኃኒቶችን በመውሰድ፣ ኢንሱሊን በመወጋት ወይም ሁለቱም በመጠቀም የምንቆጣጠረው ነው፡፡ በተጨማሪም ትክክለኛ የምግብ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ እና የመሣሠሉት ያስፈልጉታል፡፡
በደም ውስጥ የስኳር መጠን ሲያንስ የሚታዩ ምልክቶች
• ከፍተኛ ረሀብ
• ላብ ማላብ እና ማንቀጥቀጥ
• የደበዘዘ ዕይታ
• ራስ ምታትና ድብርት ይጠቀሳሉ
በደም ውስጥ የስኳር መጠን ሲከሰት/ምልክቶቹ ሲታዩ/
የስኳር መጠን በደም ውስጥ መቀነስ ምልክቶቹ መታየት በሚጀምሩበት ወቅት በአፋጣኝ የስኳር መጠንን መለካትና ከ70 በታች ከሆነ
• ለስላሳ መጠጣት ወይም ከረሜላ መብላት
• 2 የሻይ ማንኪያ ስኳር ወይም ማር መውሰድ
• በ4 ሻይ ማንኪያ ስኳር የፈላ 1 ብርጭቆ ሻይ መጠጣት
• የተወሰነ ፍራፍሬን መውሰድ
• ከላይ ከተጠቀሱት አንዱን ወዲያ መውሰድ ያስፈልጋል
የስኳር ህመምና መለኪያ መሣሪያው
በደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ከሰውነታችን የደም ናሙና በመውሰድ ለመለካት የምንጠቀምበት መሣሪያ ግሉኮሜትር ይባላል፡፡
የስኳር ህመም እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?
የስኳር ህመምን ለመቆጣጠር የሚረዱ የተለያዩ መንገዶች ያሉ ሲሆን ከሥር ተዘርዝረዋል፡-
1. የሰውነት እንቅስቃሴ
ከስኳር ህመም መቆጣጠሪያ መንገዶች መካል የሰውነት እንቅስቃሴ ዋነኛው ነው፡፡ በሰውነታችን የሚገኘውን የስኳር መጠን ዝቅ በማድረግ የህክምና ጊዜያችንን ይቆጥብልናል፡፡ በተጨማሪም ክብደታችንን እንዲቀንስ ይረዳናል፣ በሰውነታችን የሚገኘው ኢንሱሊን በተሸለ እንዲሠራ ይረዳናል፣ ለጥሩ የልብ ምት እና የደም ዝውውር ይረዳል፡፡
ማንኛውንም እንቅስቃሴ ከመሥራታችን በፊት ከሀኪም ጋር መመካከር ያስፈልጋል፡፡ ለስኳር ህመም ላለባቸው ሰዎች ከሚመከሩ የሰውነት እንቅስቃሴዎች መካከል
የእግር ጉዞ /በተቻለን መጠም በሳምንት ለ3 ጊዜ በቀን ከ20-30 ደቂቃ/ መጓዝ፡፡ በጉዞ ወቅት የጥጥ ካልሲዎችና ለእግር ጉዞ የተስማሙ ጫማዎችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ከእግር ጉዞ በተጨማሪ ዋና፣ ዳንስ፣ መረብ ኳስ ፣ ቅርጫት ኳስ የመሣሠሉት የሰውነት እንቅስቃሴዎች ጠቃሚነታቸው የጎላ ነው፡፡
2. ጤናማ አመጋገብ
የሰውነት ክብደት መጨመር፣ የስኳር ህመምን እንዳንቆጣጠር እንቅፋት ስለሚሆን ጤናማ የአመጋገብ ስልት መከተል ያስፈልጋል፡፡ ቅባትና ስኳር እንዲሁም የወተት ተዋጽኦዎችን ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ በአጠቃላይ
• በእያንዳንዱ የምግብ ክፍለ ጊዜ ኃይል ሰጪ ምግቦችን መመገብ፡፡
• አትክልት በብዛት ይመገቡ፤
• የሚመገቡትን የቅባት መጠን ይቀንሱ( የማይረጉ ቅባቶችን ለምሳሌ የሱፍ፣ የኑግና የወይራ ዘይት ወዘተ ይጠቀሙ፡፡ ቅቤና ክሬሞችን አይጠቀሙ፡፡
በመአድ ወቅት መመገብ የሚችሉት ምግቦች
• ከአትክልቶች፡ ጎመን፤ ቆስጣ፤ ጥቅል ጎመንና አበባ ጎመን ፤ ቲማቲም፤ ዱባ ፤ ካሮት፤ ፎሶሊያና ሽንኩርት
• ከፍራፍሬ፡ ሎሚ፤ ሀብሃብ ፤ የወይን ፍሬ
• ከፈሳሽ፡ አምቦ ውሃ፤ ቅባት የሌለው ሾርባ ፤ ስኳር አልባ (ስኳር የሌለው) ሻይና ቡና
• ከማጣፈጫዎች፡ ቅመማ ቅመም፤ ጨው፤ በርበሬ፤ ኮምጣጤና ሚጥሚጣ
• ከስጋ፡ የበግ የበሬ የዶሮ ስጋ ዓሣ አይብ እንቁላል ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
• ፋይበር (ቃጫ)፡- የበዛባቸው ምግቦች ያልተፈተገ ገብስ፤ ሩዝና በቆሎ፤ የማይረጋ ዘይት መጠቀም ይችላሉ፡፡
በአግባቡና በጥንቃቄ ሊወሰዱ የሚገባቸው ምግቦች
• ከአገዳ እህልና ከጥራጥሬ ዘር፡- በቆሎ፤ አጃ፤ ማሽላ፤ ባቄላ፤ ሽንብራ፤ አተር፤ ምስር፤ ቦሎቄ
• ከሥራ ሥር ድንች
• ከፍራፍሬ፡- ብርቱካን፤ ሙዝ፤ ፓፓያና አናናስ
• ከተዘጋጁና በከፊል ከተሰናዱ ምግቦች፡- የገብስ ቂጣ፣ የገብስ ቆሎ፣ ሽሮ፣ ክክ፣ የገብስ ዳቦ ህሙማኑ ወተትና የወተት ተዋፅኦ (ክሬሙ የወጣለት) በቫይታሚን ሲ እና ሌሎች ቫይታሚኖች ሚኒራሎች የበለፀጉ ፍሬዎችን ቢጠቀሙ ይበረታታሉ፡፡
የስኳር መጠን በደም ውስጥ ለሚበዛባቸው
• ስኳር ፤ ማር ከረሜላ ብስኩት ጀላቲ ቴምር ማርማላታ ዘቢብ ቼኮሌት ኬክና ስኳር ነክ ምግቦች፣ ጣፋጭና የአልኮል መጠጦች ፈፅሞ የተከለከሉ ናቸው፡፡
3. ሲጋራ አለማጨስ
ሲጋራ የሚያጨሱ የስኳር ታማሚዎች በይበልጥ እድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ አጫሾችለከፍተኛ ደም ግፊትና የሰውነት ቅባት/ኮሌስትሮል/ መጨመር በከፍተኛ የተጋለጡ ናቸው፡፡ ሲጋራ ማጨስም ለተለያዩ ሕመሞች፣ አለሰር፣ ጋንግሪንና እግር መቆረጥ አደጋ አሳልፎ ይሰጣል፡፡
4. የደም ግፊት መጠንን መቆጣጠር
የደም ግፊት መጨመር ለከፍተኛ ችግርና ስትሮክ ስለሚዳርገን ሁልጊዜ በመለካት የደም ግፊት መጠን መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
• በምግብ ውስጥ የጨው መጠንን መቀነስ፣
• የታዘዘን መድኃኒት በአግባቡ መውሰድ
• የስኳር እና የደም ግፊት መጠንነ በየጊዜው መለካት አስፈላጊ ናቸው፡፡
5. በሀኪም የታዘዙትን መድኃኒቶችን በአግባቡና ሳያቋርጡ መውሰድ መወጋትና ማስቀመጥ
ኢንሱሊን ከታዘዘለን በየቀኑ የምንወጋበት ሥፍራ ቦታ በመቀያየር /ተመሣሣይ ቦታ ከሆነ ስለሚደድርና ኢንሱሊኑ እንዳይሰራ ስለሚያደርግ/ እና በተገቢው ቦታ በማስቀመጥ፤ በአፍ የሚሰዱ መድኃኒቶች ከታዘዘሉን ደግሞ የጤና ባለሞያ በሚነግረን መሠረት መውሰድ እና ማስቀመጥ ተገቢ ነው፡፡
ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የስኳር ህመም ጉዳቶችና ጥንቃቄዎቹ
የስኳር ህመም በአግባቡ ክትትልና ቁጥጥር ካልተደረገለት በህመምተኛው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ችግሮችን ይዞ ይመጣል፡፡ ከእነዚህም መካከል
ሀ. የኩላሊት ችግር፡- በደም ውስጥ የስኳር መጠን ሲበዛ ኩላሊት ላይ ጫና በመፍጠር ለኩላሊት ህመም ያጋልጣል፡፡ በመሆኑም የደም ውስጥ ስኳርን መቆጣጠር፣ ውኃ በደምብ መጠጣትና አልኮል አለመጣጥ ያስፈልጋል፡፡
ለ. የዐይን ችግር፡- የስኳር መጠን በደም ውስጥ ሲበዛ የዕይታ ሥርዓትን ያዛባል ለዲያቤቲክ ሬቲኖፓቲለተሰኘ የዓይን ህመም ያጋልጣል፡፡የዓይን ጤናችን ለመጠበቅ የስኳር ታማሚ በየጊዜው የዓይኑን ጤና መመርመርና መጠበቅ አለበት፡፡
ሐ. የነርቭ ችግር፡- የስኳር መጠን በደም ውስጥ ሲበዛ በጊዜ ሒደት የነርቭ ህዋሶችን ይጎዳል፡፡ ይህ ደግሞ በእግርና በመሣሠሉት የሰውነት ክፍሎች የስሜት ማጣት በማጋለጥ በክንድ፣ በእጅና በእግር ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት ይሆናል፡፡
መ. የእግር ጤንነት ችግር፡-የስኳር ህመም ካልተቆጣጠሩት ለማይድን የእግር ቁስለትና ጋንግሪን ያጋልጣልና እግር እንዲቆረጥ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ምቹ የእግር ካልሲዎችና ጫማዎች/ ባዶ እግር መሔድ የተከለከለ ነው/ በማድረግ፣ በቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በመታጠብ እግርን ዘወትር በመንከባከብ ጤናን መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
ሠ. የድካም ስሜት መሰማት፡- የስኳር ህመም ከፍተኛ የድካም ስሜትን ያስከትላል፡፡ የሰውነት ክብደት መጨመር በራሱ ለስኳር ህመም ከማጋለጥ ባለፈ የድካም ስሜት እንዲበረታ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ የሰውነት ክብደት መቆጣጠር አስፈላጊ ነው፡፡
ከእነዚህ በተጨማሪ የጥርስ ጤንነት መጠበቅ፣ ሰውነታችን ላይ ለሚወጡ ቁስሎች በአፋጣኝ ትኩረት መስጠት ተገቢ ነው፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com