የጆሮ ኢንፌክሽን ወይም ፈሳሽ
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
የጆሮ እንፌክሽን በብዛት በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ ምክንያት የሚከሰት የህመም አይነት ነዉ፡፡ እንፌክሽኑ ከአዋቂዎች ይልቅ በህፃናት ላይ በብዛት የሚከሰት ሲሆን በጆሮ ዉስጥ የመቆጥቆጥና ፈሳሽ መጠራቀም ስላለዉ ብዙዉን ጊዜ ህመም አለዉ፡፡
የህመሙ ምልክቶች
የህመሙ ምልክቶች በህፃናት ላይ
• የጆሮ ህመም
• ጆሮን መጎተት/መሳብ
• እንቅልፍ ለመተኛት መቸገር
• ከበፊቱ ይልቅ መነጫነጭ መጨመር
• ባላንስ ማጣት/መንገዳገድ
• ትኩሳት
• ከጆሮ /ፈሳሽ መግል መዉጣት
• የራስ ምታት
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
በአዋቂዎች ላይ የህመሙ ምልክቶች
• የጆሮ ላይ ህመም
• ከጆሮ ፈሳሽ/መግል መዉጣት
• መስማት መቀነስ
የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?
የሚከተሉት ምልክቶች ካሉ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ
• የህመሙ ምልክቶች ከአንድ ቀን በላይ ከቆየ
• የጆሮ ህመሙ ከፍተኛ ከሆነ
• ልጅዎ የላይኛዉ የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሽን/ጉንፋን በኃላ በጣም የሚነጫነጭ ወይም እንቅልፍ የማይተኛ ከሆነ
• ከጆሮ ፈሳሽ፣መግል ወይም ደም መሳይ የሚወጣ ከሆነ
የህመሙ ምክንያቶች
የህመሙ መንስዔ በመካከለኛዉ የጆሮ ክፍል የባክቴሪያ/ቫይረስ ኢንፌክሽን በሚከሰትበት ወቅት የሚመጣ ነዉ፡፡ ህመሙ እንደ ጉንፋንና አለርጂ የመሳሰሉ ህመሞችን ተከትሎ የአፍንጫ የጉሮሮና ጉሮሮን ከመካከለኛ የጆሮ ክፍል ጋር የሚያገናኘዉ መስመር/ Eustachian tubes/ ማበጥና መዘጋት ጋር ተያይዞ ለኢንፌክሽን መጋለጥን ያመጣል/ይጨምራል፡፡
ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች
• እድሜ፡- ከ6 ወር እስከ 2 ዓመት ያሉ ህፀናቶች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸዉ፡፤
• ህፃናትን በጋራ መንከባከብ፡- ህፃናት በጋራ በሚያድጉበት ቦታ የሚዉሉ ህፃናት ለብቻቸዉ እቤት ከሚዉሉት ይልቅ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸዉ፡፡
• ወቅታዊ ሁኔታዎች፡- የጆሮ ኢንፌክሽን ጉንፋን በብዛት በሚከሰትበት በብርዳማ ወቅት በብዛት ይታያል፡፡
• የተበከለ አየር መጋለጥ፡- ከፍተኛ የአየር መበከል ወይም የሲጋራ ጢስ መታፈን ለጆሮ ኢንፌክሽን ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
የሚያመጣዉ የጎንዮሽ ጉዳት
ብዙዎቹ የጆሮ ኢንፌክሽኖች የሚያመጡት የረጅም ጊዜ የጎንዮሽ ጉዳት የለም፡፡ በተደጋጋሚ የሚመጣ እንፌክሽን ወይም ለረጅም ጊዜ የቆየ እንፌክሽን ካለ በጆሮ ዉስጥ ፈሳሽ ስለሚጠራቀም የሚከተሉት ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፡
• መስማት ያለመቻል
• የመናገር ወይም የእድገት መዘግየት
• የኢንፌክሽን መሰራጨት
• የጆሮ ታምቡር መቀደድና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
• ሙቅ ነገር ቦታዉ ላይ መያዝ፡- ይህ ህመሙን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
• የህመም ማስታገሻ መድሃኒት፡- የህክምና ባለሙያዎች የህመም ማስታገሻ መድሃኒት ሊያዝሎት ይችላል፡፡
• ፀረ ባክቴሪያ
ህመሙን እንዴት ልንከላከለዉ እንችላለን?
• ጉንፋንንና ሌሎች መሰል ህመሞችን መከላከል
• ከህክምና ባለሙያዎ ጋር ስለክትባት መነጋገር፡- ጉንፋንና እንደ ኒሞኮከስ ላሉ ባክቴሪያዎች የሚሆን ክትባት ካለ የጆሮ ኢንፌክሽኑንም ሊቀንስ ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማወያየት፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com