የማሳጅ ጥቅሞች
Author: admin
Date: 2021-06-22
የማሳጅ ጥቅሞች
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ማሳጅ ማት እጆቻችንን በመጠቀም ለስላሳ የሆኑትን የሰውነታችንን ህዋሳት በማነቃቃት የምንፈልገውን ዓይነት ውጤት ማምጣት ሲሆን ቆየት ካት የመፈወሻ መንገዶች አንዱ ነው፡፡ የማሳጅ አይነቶች እጅግ በጣም ችሎታን የሚጠይቁ ናቸው፡፡
ማሳጅ ደም በውስጡ የሚገኙ አላስፈላጊ ንጥረ ነገሮች በማስወገድ ኦክስጅንና የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮች እንዲያስገባ በማነቃቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ ማሳጅ የደም ዝውውር በመጨመር የህዋሳቶቻችንን ቀለምና የሙቀት ደረጃ የሚያሻሽል ሲሆን በቆዳ ስር የሚገኙ ጡንቻዎችንና የተለያዩ ህዋሳትን ጥንካሬ ይጨምራል፡፡ እንዲሁም የመሰባበር ፀባይ ያሳዩ የነበሩ ቆዳዎችን በማስወገድ ቆዳ ለስላሳና በቀላ የመታዘዝ ባህሪ እንዲያሳይ በተጨማሪም የቆዳን የከለር ሁኔታ ያሻሽላል፣ ዘን እንድንል ያደርጋል እና በተደጋጋሚ የማሳጅ ተጠቃሚዎች ከሆንን የጡንቻዎች ቁስለት ሲከሰት በመከላከልና ራሳቸውን በቀላ እንዲጠገኑ ያስችላል፡፡
የእጅና ክንድ ማሳጅ
ማሳጅን ከመጀመራችን በፊት የተጠቃሚውን እጆችና ክንዶች ለስለስ ባለ ጨርቅ ላይ በማስደገፍ ሙሉ ምቾት ማግኘቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ልብሶቹንም ከተለያዩ ቅባቶችና ክሬሞች ለመጠበቅ የተለያዩ ለስላሳ ወረቀት በልብሶች ጫፎች አካባቢ በመጠምጠም ንፁህ ሆኖ መቆየቱን ማረጋገጥ፡፡ የእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ሰዓቶች የተገለፁት በአማካኝ ሲሆን እያንዳንዱ እንቅስቃሴ አገልግት በሚገባ የተፈለገውን ዘና የማደረግ ተግባ መፈፀሙን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
የባት እና የእግር ማሳጅ
ማሳጅ የሚደረገውን እግር በፎጣ በመጠቅለል ሙቀት እንዲያገኝ ማድረግ በተጨማሪም እግርን እጅግ በተረጋጋና ዘና በሚያደርግ መልኩ ማሸትና ሊከሰት የሚችለውን የመኮርኮር ሁኔታ ማስወገድ አለብን፡፡ ልብሳችንን ከተለያዩ ቅባቶችና ክሬሞች መጠበቅ፡፡
የማሳጅ ቅድመ ተከተል
• በባለሙያው ጉልበት ላይ የተጠቃሚውን እግር በማሳረፍ እግር እንዲታጠፍ ካደረጉ በኋላ የኤፍሌውራጅ እንቅስቃሴን በመጠቀም ከቁርጭምጭሚት ጀምሮ እስከባት ላይኛው ክፍል ድረስ በፊት ለፊት ይሹ፡፡
• የኤፍሌውራጅን ዘዴ በመጠቀም የባትን የግራና ቀኝ ክፍል በሚያሹበትም ጊዜ በማይጠቀሙበት እጅ እግርን መደገፍዎን አይዘንጉ፡፡
• ሁለቱንም አውራ ጣቶች በመጠቀም በባት ላይ የሚገኘውን አጥንት አካባቢ በፍሪክሽን እንቅስቃሴ ይሹ፡፡
• ከላይ በተራ 2 እና 3 ላይ የተጠቀሱት እንቅስቀሴዎች ደግመው ይፈፅሙ፡፡
• የተጠቃሚውን እግር እንዲዘረጋ በማድረግ ተረከዝን በባለሙያ ጉልት ላይ በውስጠኛው የእግር ክፍልና የተቀሩትን ጣቶች በእግር የላይኛው ክፍል በማዋል ከላይ ወደ ታች በመጫን የማሳጅ አገልግሎቱን ይቀጥሉ፡፡
• ከላይ ያለውን እንቅስቃሴ በማካድ ወደታችኛው የእግር ክፍል ሲደርሱም የቁርጭምጭሚትን ዙርያና ተረከዝን በአውራ ጣትዎ በመጫን የማሸት አገልግሎቱን ያካሂዱ፡፡
• የእግር ጠርዞች በሁለቱም እጅዎ በመያዝ ጣቶችዎን በላይኛው የእግር ክፍል መዳፍዎን ደግሞ በውስጠኛው ክፍል ላይ ያሳርፉ፡፡ የኤፍሌውራጅ እንቅስቀሴም በመጠቀም ወደላይና ወደታች የማሸት ተግባርዎ ይቀጥላሉ፡፡
• በእግር የላይኛው ክፍል የሚገኙትን አጥንቶች /Metatarsals/ ለማሸት የፍሪክሽን ዘዴን ይጠቀሙ፡፡
• በእግር ላይ የሚገኝን ወጣ ብሎ የሚገኝ አጥንት በመከተል ለማሸት ይሞክሩ፡፡
• የጣቶችን መገጣጠሚያዎች ለማሸትም የፍሪክሽን ዘዴ ይጠቀሙ፡፡
• የጣት መገጣጠሚያዎች እንዲለጠጡም ጫፎቻቸውን በመያዝ ይሳብዋቸው፡፡
• እጆችን በማገጣጠም ከእግር በላይ በማዋል የእግር ጣቶችን ወደ ታች በማጠፍ ከታች የሚገኘውን የእግር መዳፍ ይሹ፡፡
• የእግርን ግራና ቀኝ በሁለቱም እጆች በመያዝ ጨመቅ ለቀቅ እያደረጉ እግርን ዘና ያድርጉ፡፡
• በማሸት ዘዴ በመላው የውስጠኛው የእግር ክፍል ላይ በማዋል የፍሪክሽን ዘዴ ይጠቀሙ፡፡
• በፊት ለፊትና በኋላ በኩል የሚገኘውን የቁርጭምጭሚት አካባቢ አውራ ጣትዎንና የተቀሩትን ጣቶች በፍሪክሽን እንቅስቃሴ ማሸት ያስፈልጋ፡፡
• በአንድ እጅ ተረከዝን በሌላው የእግርን የላይኛው ክፍል በመያዝ ወደአንድ ጎን በሶስት ጊዜ ወደ ሌላኛውም ጎን ለሶስት ጊዜ ያሽከርክሩት፡፡ በዚህም ወቅት ያለንን ግፊት መጠቀም የቁርጭምጭት አካባ መገጣጠሚያዎች ዘና እንዲሉ ያደርጋል፡፡
• እግርን ከላይ በተጠቀሰው መንገድ በመያዝ ሊሄድ እስከሚችለው ርቀት ይሳቡት፡፡
• በዚህ ደረጃም በተቻልዎት መጠን ወደኋላ በመግፋት የቁርጭምጭሚት አካባቢ መገጣጠሚያዎች ዘና እንዲሉ ያድርጉ፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com/%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B5-%E1%88%9A%E1%8A%AB%E1%8A%A4%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%89%A3%E1%88%85%E1%88%8D-%E1%88%95%E1%8A%AD%E1%88%9D%E1%8A%93-106520591088973/
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com