የነርቭ ህመም ምልክት ለታየበት ሰው የሚረዳ የቤት ውስጥ ህክምና
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ

የነርቭ ህመም የጉዳት ምልክቶች
1.መደንዘዝ:- ስሜታዊ ነርቮች/sensory nerves/መጎዳታቸውን የምናውቅበት የመጀመሪያው ምልክት የመደንዘዝ እና የመውረር ስሜት በእጅ፣ በጣት፣ በእግር፣ እና በእግር ጣቶች ላይ ሲፈጠር ነው። ስሜታዊ ነርቮች ስራቸው የስሜት መልእክት መላክ ሲሆን ጉዳት ሲያጋጥማቸው ቆይቶ ወደ መደንዘዝ የሚቀየር የመውረር ስሜት ይሰማናል። በጊዜው ተገቢ ህክምና ካላገኘ ይህ ስሜት ወደ ሌሎች የሰውነት አካሎች ሊዛመት ይችላል። ህመሙ ከጊዜ ጋር እየጨመረ የቀን ከቀን ኑሮአችንን ያስተጓጉላል። እጅ እና እግር ላይ ለሚፈጠር የመደንዘዝ ስሜት ሌሎች መንስኤዎች እግር እና እጅ ላይ የተፈጠረ ከፍተኛ ጫና፣ ለብርድ መጋለጥ፣ እንቅስቃሴ የሌለበት የአኗኗር ዘይቤ እና የቫይታሚን ቢ12 እና ማግኒዚየም እጥረት ናቸው።
2. ህመም:- ሌላ የነርቭ ህመም ምልክት የሚሰነጥቅ ወይም የሚያቃጥል የህመም ስሜት ነው። የዚህ አይነት ስሜት እጅ እና እግር ላይ የሚፈጠር ሲሆን ከሌላ የህመም ስሜት ይለያል። ህመሙ የሚፈጠረው ስሜታዊ ነርቮች ላይ በተፈጠረ ጉዳት ነው። ስሜት በአግባቡ ከአእምሮ ወደ ቆዳ መተላለፍ ካልቻለ የተጎዳው ቦታ ላይ ከፍተኛ ህመም ሊሰማን ይችላል። የህመሙ ቦታ በተጎዳው ክልል ዙሪያ ብቻ ወይንም ሰፊ የሰውነት ክልል ላይ ሊፈጠር ይችላል። ህመሙ ብዙ ጊዜ በምሽት ይባባሳል። ከነርቭ ጉዳት ውጪ የስኳር በሽታ፣ የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ወይም የጀርባ አጥነት ሰረሰር ላይ የተፈጠረ ጉዳት ለከባድ የህመም ያጋልጠናል።
3. የጡንቻ ድካም:- ጡንቻ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርገውን መልእክት የሚያስተላልፉ ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ ድካም ይፈጥራል። አልፎም ጡንቻን የመቆጣጠር ችሎታ ሊያሳጣ ይችላል። ለጡንቻችን የሚላከው መልእክት በአግባቡ ካልተላለፈ መራመድ እንቸገራለን። በእጃችን እቃዎች ለማንሳት እና ጭብጥ አድርጎ መያዝ ይከብደናል። በነርቭ ጉዳት ምክንያት ጡንቻ ጥቅም ላይ የሚውልበት ጊዜ ሲቀንስ እራሱ እየደከመ ይመጣል። ጡንቻ መዳከም ከነርቭ ጉዳት ውጪ እንደ ፓርኪንሰን በሽታ፣ የዲስክ መንሸራተት፣ ስትሮክ የመሳሰሉ ህመሞች መንስኤው ይሆናሉ።
4. የጡንቻ መሸማቀቅ:- የእንቅስቅሴ ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ ሊያመጣ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ በራሱ የተጎዱት ነርቮች ላይ በሚፈጥረው እንቅስቃሴ ጉዳቱን ሊያባብስ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ የሚፈጠረው የእንቅስቃሴ ነርቮች በብዛት ሲሰሩ ነው። የመሸማቀቅ ስሜት ክብደቱ ቀላል፣ መሃከለኛም ወይንም በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል።
5. የላብ ችግር:- የሰውነት አካልን የሚረዱ ነርቮች ሲጎዱ አውቶኖሚክ ኒውሮፓቲ የሚባል ህመም ሊያስከትል ይችላል። አውቶኖሚክ ነርቮች ሲጎዱ የላብ ችግር ሊፈጥር ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ላብ ሲፈጠር ሌሎች ላይ ደግሞ የላብ መቀነስ ይታያል። ላብ በአግባቡ ካልመነጨ ሰውነታችን ሙቀቱን በአግባቡ መቆጣጠር አይችልም። በከፍተኛ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት ችግሩ ይገዝፋል።
6. ሽንት ቤት መመላለስ:- የሽንት ፊኛ ሽንትን በደንብ እንዲይዝ ብዙ ነርቮች አብረው መስራት አለባቸው።
የነርቭ ጉዳት ሲፈጠር የሽንት ፊኛ ሽንትን ቶሎ ቶሎ ለማስወገድ ይሞክራል። የነርቭ ጉዳት የሽንት ፊኛ ጡንቻዎች የሚያደርጉትን መኮማተር እና መላላት በተገቢው መልኩ እንዳያደርጉ ያስተጓጉላል። የሽንት ፊኛ ችግር ሌላ መንስኤ ሊኖረው ይችላል። ልጅ በወለዱ እናቶች እና የስኳር በሽታ ታካሚዎች ላይ የሚፈጠር ችግር ነው።
7. ከባድ ራስምታት:- ኤሌክትሪክ ንዝረት የሚመስል አጭር ጊዜ የሚቆይ ከባድ ራስምታት የነርቭ ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል። ህመሙ የኦክሲፒታል ኒውራልጂያ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል። ኦክሲፒታል ኒውራልጂያ አንገት ላይ ያለ የነርቭ መቆንጠጥ በሽታ ነው። ህመሙ የላይኛው አንገት ክፍል ወይም ጭንቅላት ጀርባ ላይ ይፈጠራል።
8. ሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር:- የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር ወይም መንገዳገድ ሌላ የነርቭ ጉዳት ምልክት ነው። ወድቀው ሊጎዱ ስለሚችሉ ይህን ምልክት ችላ ማለት የለብዎትም። የነርቭ ጉዳት አእምሮ የሰውነትን እንቅስቃሴ በአግባቡ እንዳይቆጣጠር ያደርጋል። ይህ ሁኔታ ወድቀው እንዲጎዱ ሊያደርግ ይችላል። የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር የፓርኪንሰን ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል።
• በቤት ውስጥ ልናደርጋቸው የሚገቡ ህክምናዎችን እንሆ
1. የሳማ ስር፣ቅጠል፣ግንድ እና አበባውን ለያይቶ በማድረቅ እያንዳንዱን ለየብቻ በመውቀጥ ( በመፍጨት) ከሁሉም አንዳንድ ስኒ እየተለካ ከ አንድ ኪሎ ወለላ ማር ጋር ተለውሶ በየአንድ ቀን ልዩነት ህመም የሚሰማን ቦታ መቀባት
2.በነጭ ሽንኩርት እንፋሎት በቀን ሁለት ግዜ መታጠን
3.አንድ ፍሬ ነጭ ሽንኩርት ቆርጥመው በሎሚ ወይንም በግመል ወተት በቀን ሁለት ግዜ እየተጉመጠመጡ መዋጥ ይህም ለአንድ ሳምንት መቀጠል አለበት
4.አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ከ አምስት ጠብታ ጥቁር አዝሙድ ጋር እየተደባለቀ ጠዋት ጠዋት ለአንድ ወር መውሰድ
• መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com/%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B5-%E1%88%9A%E1%8A%AB%E1%8A%A4%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%89%A3%E1%88%85%E1%88%8D-%E1%88%95%E1%8A%AD%E1%88%9D%E1%8A%93-106520591088973/
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com