የአባሽ ኮሶ
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
የአባሽ ኮሶ ዛፍ ሁለት አይነት ነው ፡፡ ለሰው መድሀኒትነት የሚውለው ከሴቴ ኮሶ ዛፍ ሲሆን እሱም ሁለት አይነት ነው ፡፡ ከሴቴ አበባውን ቆርጦ በጥላ ቦታ ማድረቅ እና ከመተሬ ፍሬ ጋር የሁለቱን ውህድ ዱቄት ማዋሀድ የተዘጋጀውን ውህድ ከሶስት ቀናት በፊት በውሃ ወይም በአሬራ ለውሶ ከድኖ ማቆየት ለአንድ ሰው ከሁለት እስከ አራት የሾርባ ማንኪያ ከአሬራ ወይም ከውሃ ጋር በጥብጦ በአንድ ትንፋሽ መጠጣት ፡፡
መድሃኒቱን በአንድ ግዜ መወሰድ ለሚከብደው ሰው በትንሽ በትንሹ መውሰድ ፣ ፓፓያ ቀቅሎ በሱ መውሰድ ፣ በዱባ፣ በሳማ ወይም በሞቀ የተልባ ውሃ በጥብጦ መውሰድ ፡፡ ወድያውኑ ቡና በቅቤ መጠጣት መድሃኒቱን ከወሰዱ በኋላ ለግማሽቀን ያህል ምግብ አለመብላት በተደጋጋሚ ቡና በጨው ወይም በቅቤ ያለ ስከኳር መጠጣት ፡፡
በተደጋጋሚ ተቅማጥን በሚያስከትልበት ግዜ ትናንሽ የኮሶ ትሎች እና ንፋጭ ነገሮች ከሆድ ውስጥ መውጣት ይጀምራሉ ፡፡
የኮሶ ትሉ በተቅማጥ ከወጣ በኋላ ምግብ በልቶ እረፍት ማድረግ ተገቢ ነው ፡፡ከወተት እና ከጥሬ ስጋ ውጭ ማንኛውንም የበሰለ ምግብ መመገብ አስፈላጊ ነው ፡፡
የአባሽ ኮሶን ምድሃኒት መውሰድ የኮሶ ትልን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ትላትሎችንም ከሆድ ውስጥ ያስወግዳል ፡፡ይህንን መድሃኒት እንደየ ስፈላጊነቱ ቢቻል በወር አንዴ ቢወሰድ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com/%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B5-%E1%88%9A%E1%8A%AB%E1%8A%A4%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%89%A3%E1%88%85%E1%88%8D-%E1%88%95%E1%8A%AD%E1%88%9D%E1%8A%93-106520591088973/
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com