ነጭ ሽንኩርት እና ማር
Author: admin
Date: 2021-06-16
ነጭ ሽንኩርት እና ማር
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ፍቱን መድሃኒት
ነጭ ሽንኩርትና ማር ለማዘጋጀት በጣም ቀላል ሲሆኑ በርካታ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ያስችላሉ፡፡
መላ አንድ
አዘገጃጀት፦
• ሁለት ወይም ሶስት ነጭ ሽንኩርት እና አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር፤
• ነጭ ሽንኩርቱን በመላጥ ማድቀቅ እና ከማሩ ጋር በመቀላቀል በባዶ ሆድ መውሰድ።
• ይህን ሲያደርጉ የበሽታ መከላከል አቅምዎም ይጎለብታል ጤንነትዎንም ይጠብቃሉ።
• ጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛን በማከምም ጤንነትዎ የተጠበቀ ይሆናል።
• ከዚህ በተጨማሪም ነጭ ሽነኩርትን ከሌሎች ነገሮች ጋር መጠቀምም ይችላሉ።
• ለዚህም አምስት ፍሬ ነጭ ሽንኩርት፣ አንድ የሾርባ ማንኪያ ደቀቅ ብሎ የተዘጋጀ ዝንጅብል፣ ተለቅ ያለ ሎሚ እና አንድ የሚጥሚጣ ቀይ ቃሪያ፤
መላ ሁለት
አዘገጃጀት፦
• በቅድሚያ ከ350 እስከ 500 ሚሊ ሊትር የመያዝ አቅም ያለው ጆግ ማዘጋጀት፤
• ከዚያም ነጭ ሽንኩርቱን በማድቀቅ መገልበጥ ቀጥሎ ቃሪያውን መጨመርና በላዩ ላይ የደቀቀውን ዝንጅብል በማድረግ ሎሚውን ላዩ ላይ መጭመቅ።
• ከቻሉ ኮምጣጤ ላዩ ላይ በመጨመር ውህዱን ማቀዝቀዣ ውስጥ ማስቀመጥና በየቀኑ መጠቀም።
• በዚህ መልኩ ቢጠቀሙት ከበርካታ በሽታዎች ራስዎንና ቤተሰብዎን መጠበቅና በተለይም እንደ ጉንፋን ያሉ በሽታዎችን መከላከልና ማከም ይችላሉ።
• ነጭ ሽንኩርትን የሚያዘጋጁት ምግብ ላይ በመጨመር መመገብም ይችላሉ።
ይህም በርካታ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ያስችልዎታል፥ ምን ጊዜም ቢሆን ግን ከተጠቀሰው መጠን በላይ እንዳይጠቀሙ ይመከራል።
ይህን ማድረግዎ ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር፣ በሰውነት ውስጥ የኮሊስትሮል መጠንን ለመቀነስና የልብና ተያያዥ የጤና እክሎችን ለመቀነስ ይረዳወታል።
ከፍተኛ ትኩሳት፣ ጉንፋን፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ሳል፣ በተባይ ንክሻ የሚመጣ በሽታን ለማከመም ፍቱን መድሃኒት እንደሆነ ይነገራል።
ከዚህ ባለፈም እንደ ስኳር ያሉ በሽታዎችን ለመቆጣጠርና ለማከም ይረዳል።
ዘወትር ሙሉ ጤንነት እንዲሰማዎት እና በሙሉ ህይል እንዲሰሩና እንዲንቀሳቀሱም ያግዛልና ይጠቀሙት። አሁኑኑ ይሞክሩት…
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com