ቁስለትን ለመከላከል የሚረዱ ምግቦች
Author: admin
Date: 2021-06-15
ቁስለትን ለመከላከል የሚረዱ ምግቦች
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ከጥንቃቄ ጉድለትም ሆነ ሳይታሰብ በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚከሰቱ አደጋዎች መቼም በሰውነታችን ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱ የማይቀር ነው። ተከስቶ ሲገኝ ታዲያ ቁስሉ ቶሎ እንዲሽር የተለያዩ ዘዴዎችን እና አማራጮችን መውሰዳችንም እንዲሁ። ከእነዚህ ቁስል በቶሎ እንዲድን ከሚረዱ ዘዴዎች መካካልም በተፈጥራዊ መንገድ የተለያዩ ምግቦችን ቁስሉ ላይ በማድረግ እና በመመገብ ፈውስ ማግኘት ይቻላል። እስኪ ብንመገባቸው ቁስል በቶሎ እንዲያገግም ከሚረዱን መካካል ዋና ዋናዎቹን አናስቃኝዎ።
1.ማር፦
ማር እጅግ ጠቃሚ የምግብ አይነት እንደሆነ ይታወቃል። ጣፋጩ ማር በውስጡ ባሉት እጅግ በርካታ የቫይታሚን አይነቶች፣ አሚኖ አሲድ፣ እና ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮች ሳቢያ ቁስል ቶሎ እንዲሽር የማድረግ ፣እብጠትን እና የማቃጠል ስሜትን የማስታገስ አቅሙ ከፍተኛ እንደሆነ ይነገርለታል። በተጨማሪም ማር ያለው ተፈጥሯዊ አንቲባዮቲል ባህሪ ቅስልእንዳያመረቅዝ እና ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር ያግዛል።
2.የወተት ተዋፅኦዎች፦
እንደ ወተት እርጎ ያሉት የወተት ተዋፅኦዎች በተፈጥሮ በተቀዳጁት ከፍተኛ የፕሮቲን እና ዚንክ መጠን ቁስል በፍጥነት እንዲድን የማድረግ አቅም አላቸው። በመሆኑም እንደእነዚህ ያሉትን የምግብ አይነቶች ቁስል በሰውነታችን ላይ በሚከሰትበት ወቅት እንድናዘወትር ይመከራል።
3.የስጋ ውጤቶች፦
እንደ ወተት ሁሉ ስጋም በውስጡ የያዘው ፕሮቲን እና ዚንክ በፍጥነት ቁስል እንዲደርቅ ያሰችላል። በተለይም በተለያየ ሁኔታ የመቁሰል አደጋ ያጋጠማቸው አሳ፣ የጥጃ እና የዶሮ ስጋን አዘውትረው ቢመገቡ በቶሎ እንዲያገግሙ ያስችላቸዋል ነው የተባለው። ጥራጥሬ፣ ለውዝ፣ ምስር የመሳሰሉትን መመገብም ቶሎ ቁስለትን ለማዳን የሚረዱ አማራጮች ናቸው።
4.ቫይታሚን ሲ፦
ቫይታሚን ሲ ለበርካታ የሰውነት ተግባራት ጥቅም ይሰጣል። በተለይም ቁስልን ጨምሮ በሰውነታችን ላይ የሚታዩ የጭረት ምልክቶች፣ ሸፍታ፣ የቆዳ መበለዝን ሳይቀር ለማጥፋት ይረዳል።
በመሆኑም መሰል ችግር ያለባቸው እንደ ሎሚ፣ ብርቱካን፣ መንደሪን፣ ዘይቱን፣ እንጆሪ፣አናናስ ከፍራፍሬ እንዲሁም ቲማቲም፣ ስፒናች፣ ጎመን የመሳሰሉትን ከአትክልት ዝርያዎች እንዲመገቡ ነው የሚመከረው።
5.ስኳር ድንች፦
ስኳር ድንች የቫይታሚን ኤ፣ ቢ እና ሲ አይነተኛ መገኛ በመሆኑ እና ተፈጥሯዊ አንቲኦክሲዳንቶችን በመላበሱ አዘውትረን
መመገቡ ቁስልን በቶሎ ለመከላከል ያስችለናል።
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com