የኮሶ ትል ህመም
Author: admin
Date: 2021-06-08
የኮሶ ትል ህመም
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
የኮሶ ትል ነጭ ወይም ቢጫ መሰል መልክ ያለው ቀጭን ትል ሲሆን በእንስሳት አንጀት ውስጥ ነው ዋነኛው መኖሪያው፡፡ እንስሳቱ በሚግጡበት ጊዜ ወይም የተበከለ ውሃ በሚጠጡበት ጊዜ ወደ ሰውነታቸው ውስጥ ይገባል፡፡ የኮሶ ትል የህይወት ጊዜው እንቁላል፤ ላርቬ እና ትል (ትል ሲሆን እንቁላል መጣል እና መራባት ይችላል) በመባል በሶስት ይከፈላል፡፡ የኮሶ ትል ላርቬ (በእንቁላል እና በትል መካከል ያለው) በእንስሳቱ ጡንቻዎች ውስጥ ስለሚገባ ጥሬ ስጋ ስንመገብ ከስጋው ወደ እኛ ሰውነት ይገባል፡፡
አባቶቻችን በጦርነት ጊዜ ምግብ ሲያበስሉ በሚወጣው ጭስ ጠላት ያሉበትን እንዳያውቅ ብለው ጥሬ ስጋን መመገብ እንደጀመሩ ይነገራል፡፡ አሁን ባህላችን የሆነው ጥሬ ስጋ መብላት ለኮሶ ትል እንድንጋለጥ አድርጎናል፡፡
ኮሶ እንዴት ይይዛል?
ኮሶ በአብዛኛው የሚይዘን ጥሬ ስጋ (የበሬ/የላም)፤ ጥሬ አሳ ወይም ጥሬ የአሳማ ስጋ በመብላት ነው፡፡ አልፎ አልፎም በተበከለ ውሃ ወይም በኮሶ ትል በተያዙ እንስሳት እዳሪ ምክንያት የኮሶ ትል ይይዘናል፡፡
የኮሶ በሽታ ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?
የኮሶ ትል ከተሸከመው እንስሳ ሰውነት ጋር በደንብ ተዋህዶ ምንም ምልክት ሳያሳይ ለረጅም ጊዜ በአንጀት ውስጥ መኖር ይችላል፡፡አንድ የኮሶ ትል በሰው አንጀት ውስጥ እሰከ 20 አመት መኖር ይችላል እንዲሁም ከ10 ሜትር በላይ ማደግ ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ የሚያስከትላቸው የህመም ምልክቶች
ሀይለኛ የሆድ ቁርጠት (በተለይ ከእንብርት በላይ ጭብጥ አርጎ የሚይዝ)
ተቅማጥ
ማቅለሽለሽ ወይም ማስመለስ
ድካም ድካም ማለት
ምግብ በጣም መብላት ወይም የምግብ ፍላጎት መጥፋት
ክብደት መቀነስ
በሰገራ ውስጥ የኮሶ ትል ማግኘት (ነጣ ያለ ወይም ቢጫ መልክ ያለው፤ ጠፍጣፋ ቅርፅ ያለው)
የኮሶ ህመም ምልክቶችን ካየን ወደ ሃኪም ዘንድ በመሔድ ምርመራ ማድረግ ይመከራል፡፡ ሃኪሙም የሰገራ ምርመራ እና ሌሎች ምርመራዎችን ካደረገልን በኋላ መድሃኒት ይታዘዝልናል፡፡ መድሃኒቱን በትክክል እና በአግባቡ ከተጠቀምን ኮሶ ከሰውነታችን ውስጥ ይጠፋል፡፡ነገር ግን ነፍሰ ጡር ሴት የኮሶ መድሃኒት መውሰድ የለባትም፡፡
የኮሶ ትልን እንዴት መከላከል ይቻላል?
ከምግብ በፊት፤ መታጠቢያ ቤት ከተጠቀምን በኋላ እና ከእንስሳት ጋር ከተገኛኘን በኋላ እጃችንን በውሃ እና በሳሙና በደንብ መታጠብ
የኮሶ ትል እንዳይዘን በተቻለ መጠን በደንብ የበሰለ ስጋ፤አሳ እና አሳማ ነው መመገብ ያለብን፡፡
ንፁህ የሆነ ወይም የታከመ ውሀ ብቻ መጠጣት
በቤታችን ውስጥ ውሻ የምናሳድግ ከሆነ የኮሶ መድሃኒት በእንስሳ ሃኪሞች እንዲሠጣቸው ማድረግ፡፡ በተለይ ልጆች ካሉን የኮሶ ትሉ ከውሻ ወደ ህፃነቱ እንዳይተላለፍ መጠንቀቅ አለብን፡፡
በተለይ ከአሳማ ስጋ የሚመጣው የኮሶ ትል ወደ አእምሮ ውስጥ በመግባት ነርቮቻችንን ማበላሸት ስለሚችል አሳማ ስጋ ስንበላ እና የአሳማ እዳሪ የምንነካ ከሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ፡፡
በተለምዶ ደግሞ ፓፓያ ወይም አናናስ መብላት ወይም ጁሱን መጠጣት የኮሶ ትል እንዳይዘን ይከላከላል ተብሎ ይታመናል፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com