በእባብ ለተነደፈ ሰው
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
እባብ መርዛማ ወይም መርዛማ ያልሆኑ ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ ፡፡ በተለይ በቆላማ አካባቢ የሚገኘው መርዛማ እባብ ነው ፡፡
በእባብ የተነደፈ ሰው ምን ማድረግ አለበት ?
›› የተነደፈው ቦታን በፍጥነት ካሰሩ በኋላ በንፁህ ምላጭ የተነደፈውን ቦታ መርዙ እስከሚወጣ ማድማት ይህን ካደረጉ በኋላ በውሃ እና በሳሙና ማጠብ ፡፡
›› አውራ ዶሮ በኩስ ማውጫው በኩል ከተነደፈው ቦታ ጋር አጣብቆ መያዝ መርዙን ወደራሱ ስቦ በሚያጣው ሰአት ዶሮ ይሞታል ያኔ መርዙን አውጥቶታል ማለት ነው፡፡
›› ታማሚው ብዙ ውሃ ፣ ወተት እና እርጎ ( አጓት) በመጠጣት እንዲያስመልስ ማድረግ፡፡
›› በእለቱ ምግብ አለመመገብ፣ እንቅልፍ አለመተኛት፣ሲሻለው የጤናዳም ቅጠል እና ፍሬውን ከውሃ ጋር ፈጭተው ጭማቂውን በአንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ጋር በጥብጦ በየሁለት ሰአት መጠጣት፡፡
››አቶች (አቱች)
በውኃማ አከባቢ እና በብዛት በክረምት ወቅት ለምልማ ትገኛለች በደጋ እና በወይና ደጋ በብዛት ትገኛለች።
በጓሮ፤ በሜዳማ ቦታ፤ በእርሻ ቦታ ወዘተ መገኛዋ ነው።
አቶች ለተለያየ በሽታ መፍትሔ ባለቤት ስትሆን!
ለምሳሌ የጥንት እናቶቻችን፦
#ለቶንሱል ቅጠልዋን ይጠቀሙባታል።
#ሆድ ውስጥ ለተሰራ ሥራይ ይጠቀሙባታል።
#እንዱሁም ለሚቃዥ ህጻን ሥሯን በማሰር ይጠቀሙባታል።
ዛሬ ደግሞ በመርዛማ እባብ ለተነደፈ ሰው መፍትሔ ስትሆን እንመለከታለን።
በእባብ ላለመነከስ ከዚህ በፊት እንዳየነው የዕፀ ዘዌ ሥር አስሮ መያዝ እምደሚከላከልልን ሁሉ!
#የአቶች ሥር በማንኛውም ሰዓት በመንቀል!
አኝከው አላምጠው ውኃውን ሲውጡት ወድያውኑ መርዙ ወደላይ በማስታወክ እንዲወገድ ይሆናል።
የዕፅዋ መደብ፦ መረር የምትል ከመርዛማ እጽዋቶች ውጭ ናት!

መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com
https://t.me/kidusmikaelhikmna