በመርዛማ ሸረሪት ለተነደፈ ሰው የሚረዱ የቤት ውስጥ መፍትሄዎች
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ

ሸረሪቶች በጀርባቸው ላይ ግራጫ ወይም ቡናማ የሆኑ ሸንተረሮች አሏቸው፡፡ ምግባቸውን ፍለጋ አብዛኛውን ጊዜ በለሊት ይዘዋወራሉ፡፡ እጅግ መርዛማ ስለሆኑ መጠንቀቅ አለብን፡፡ በነዚህ ሸረሪቶች የተነደፈ ሰው የሚያሳየው ምልክት ከብላክ ዊደው ሸረሪት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ከፍተኛ ህመም፣ ላብ፣ ማንቀጥቀጥ፣ ድካም እና ከእንቅስቃሴ መገደብ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው፡፡ ፈነል ዌብስ(Funnel webs) ሸረሪቶች በመሬት ላይ ካሉ በጣም አደገኛ እንስሳት ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው፤ ምክንያቱም መርዛቸው አንድን ሰው በ15 ደቂቃ ውስጥ መግደል ስለሚችል ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በሳር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ መርዛቸው በጣም አደገኛ በመሆኑ የአንቲዶት(antidote) ህክምና በፍጥነት ካላገኘ ለሞት ይዳርጋል፡፡ ወንዱ ሸረሪት የበለጠ መርዛማ ነው፡፡ የአንቲዶት(antidote) መድኃኒቱ ከራሳቸው ከሸረሪቶቹ የሚገኝ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ ይታደናሉ፤ ለአንድ ሰው የሚሆን መርዛቸውን ማርከሻ መድኃኒት ለመስራት እስከ ሃምሳ ጊዜ መርዛቸውን ማለብ ወይም ማስተፋት ያስፈልጋል፡፡
==ማስጠንቀቂያ!==
የተለያዩ ትናንሽ ነገር ግን አደገኛ ፍጡራን ለምሳሌ መርዛማ ሸረሪቶችና እንቁራሪቶች በተለያዩ የሚታወቁ አካባቢዎች እንደሚገኙ የሚታወቅ ቢሆንም፣ ከተለያዩ ሸቀጦችና ምርቶች ጋር ማለትም አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎችና ሌሎች የዕፅዋት ውጤቶች ጋር በተለያዩ የመጓጓዛ መንገዶች ማለትም በመርከብ፣ በአውሮፕላንና በመኪናዎች አማካኝነት ከአንዱ የዓለም ዳርቻ ወደ አንዱ ባጋጣሚና በድንገት ወይም ሆን ተብሎ ስለሚሰራጩ፣ እዚህ ቦታ ይገኛሉ ተብለው የሚጠቀሱ ፍጡራን ሌላ አካባቢ ላይም ሊያጋጥሙ ይችላሉ፤ ለምሳሌ ከደቡብ አሜሪካ ወደ ተለያዩ አገሮች የሚጓጓዙ እንደ ሙዝ ያሉ ምርቶች መርዛማ ሸረሪቶችን በየአገሩ ሊያዳርሱ ይችላሉ፤ ይህ ሁኔታ በትክክልም የተለያዩ አገሮች ላይ ተከስቶ ታይቷል፡፡ ለምሳሌ በእንግሊዝ አገር ያልነበሩ መርዛማ ሸረሪቶች ከብራዚል አገር ወደ እንግሊዝ ከሙዝ ጋር ተጓጉዘው ገብተዋል፡፡ ይህ ሁኔታ በሌሎች ትናንሽና አደገኛ የእንስሳ አይነቶች እንዲሁም በሌሎች አገሮችም ላይ ሊያጋጥም ይችላል፤ ስለዚህ ምንጊዜም የሚያዋጣን መጠራጠርና ጥንቃቄ መውሰድ ነው፡፡
አደገኛ እና መርዛማ ሸረሪት በወይናደጋ ወይም በቆላ አንዳንድ አካበቢዎች ትገኛለች፡፡
ይህች ሸረሪርት ከምናውቃቸው ሸረሪቶች ስለምትለይ የተነደፈው ሰው በቶሎ የዘመናዊም ሆነ የባህላዊ ሃኪም ጋር መታከም ይኖርበታል ፡፡
በቤት ውስጥ እንዴት ልናክመው እንችላለን
1. የጤናዳም ፍሬውን እና ቅጠሉን በመፍጨት ለብ ባለ ንፁህ ውሃ በጥብጦ በማጥለል ጭማቂውን ከማር ጋር አዋህዶ መጠጣት፡፡
2. ባለ ወተቱን ቁልቋል የተነደፈው ቦታ ላይ መቀባት እና
3. በሎሚ እና በነጭ ሽንኩርት በደንድ ማሸት ከህመሙ ለማገገም የሚረዱ የቤት ውስጥ መፍትሄዎች ናቸው፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com