የተስቦ በሽታ
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ

ተስቦ ማለት በሌላ አጠራር ታይፈስ ይባላል ፡፡ የተስቦ በሽታ ሁለት ዓይነት ሲሆን የመጀመሪያው በወረርሽኝ መልክ የሚሰራጨውና በቅማል አማካኝነት ወደ ሰው የሚተላለፈው(Epidemic Typhus) ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ በአካባቢ የሚወሰንና አይጦች ላይ በሚገኙ ቁንጫዎች አማካኝነት የሚተላለፍ (Endemic/Murine Typhus) ነው፡፡
ሁለቱም ከንፅህና ጉድለት የሚመጡ ሲሆን በተለይ ተፋፍገው በሚኖሩ ሰዎች መካከል በይበልጥ ሊከሰት ይችላል፤ አብዛኛውን ጊዜ በእስር ቤቶችና ከተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በኋላ በአንድ ላይ ተፋፍገው በሚጠለሉ ተጎጂዎች ወይም ስደተኞች ላይ በስፋት ይታያል፡፡ ሁለቱም የሚያሳዩት ምልክት ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽ እና ከአራት ቀን በኋላ ሽፍታ ከብብት በመነሳት ወደ ደረት፣ ሆድና ዳሌ መስፋፋት ነው፡፡ በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ከ12 ቀናት በኋላ ማገገም ሊጀምሩ ይችላሉ ወይም ራስን መሳትና ሞት ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ እንዲህ ያሉ የተስቦ በሽታዎች መድኃኒቱ ባልነበረበት የቅርብ ዘመን እንኳን የሚልዮኖችን ህይወት ቀጥፈዋል፡፡ ሕክምናው አንቲባዮቲክ ሲሆን ክትባትም አለው፡፡
መድኃኒቱ የተሰጣቸው ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በሁለትና ሶስት ቀን ውስጥ የመሻል ስሜት ይኖራቸዋል፡፡ በሽታው እያለባቸው ሕክምናውን ማግኘት ያልቻሉ ሰዎች ለሳምንታት የሚቀጥል ትኩሳት ይኖራቸዋል እየጠነከረ ሲሄድም ከፍተኛ ጉዳት በሰውነት ላይ በማስከተል እስከሞት ያደርሳል፡፡
በሽታው የሚተላለፍባቸው መንገዶች
ባክቴሪያው በተበከለ ምግብና መጠጥ አማካኝነት ወደ ሰውነት ከገባ ራሱን በማራባት ወደ ደምና ደም ዝውውር በሚዘልቅበት ጊዜ ሰውነት ትኩሳትና ሌሎች ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራል፡፡
ራሳችንን ከበሽታው እንዴት እንከላከል?
በበሽታው የተያዙ ሰዎች ከሕክምና በኋላ በሐኪም የሚታዘዝላቸውን መድኃኒት ሙሉ በሙሉ መጨረስ ይኖርባቸዋል፡፡ ከመፀዳዳት በኋላም በሳሙናና በውኃ እጅን ሙልጭ አድርጎ ማጠብ ያስፈልጋል፤ በተጨማሪም መድኃኒት ወስደው የመሻል ስሜት ቢኖርም ባክቴሪያው ከሰውነት ጠርቶ ላይወገድ ይችላል፤ ስለዚህ በሽታው ተመልሶ ሊመጣ ከመቻሉም በላይ በሽታውን ወደ ሌላ ሰው የማስተላለፍ ሁኔታ ይኖራል፡፡ ሰዎች ከባክቴሪያው ነፃ ለመሆናቸው ሐኪም ዘንድ ቀርበው በድጋሚ ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
መፍትሔ
ምግብና መጠጥ በባክቴሪያው ሊበከሉ የሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ ትኩረት በማድረግ መከላከል ወይም ከተበከሉ አካባቢዎች ሊመጡ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡ የምግብና መጠጥ ምንጮችን አለመጠቀም ነው፡፡
ተጨማሪ ጠቃሚ ምክሮች
• የታሸገ ውኃ መጠቀም፣ የታሸገ ማግኘት ካልቻሉ ደግሞ ከመጠጣትዎ በፊት ውኃውን በሚገባ ማፍላት፡፡
• ምግብ በደንብ የተቀቀለ ወይም የተጠበሰ መሆን አለበት፤ በትኩስነቱም መመገብ አለብን፡፡
• መላጥ የማይችሉ ፍራፍሬዎችን ወይም በደንብ ያልበሰሉ ቅጠላቅጠሎችን አለመመገብ፤ በተለይ ጥሬ የሚበሉ ቅጠላቅጠሎች በቀላሉ ሊበከሉ ስለሚችሉ ተገቢውን የማፅዳት ስራ ካከናወኑ በኋላ መመገብ፡፡
• ተልጠው የሚበሉ ፍራፍሬዎች ራሳችን ልጠን መብላት፤ ነገር ግን ከመላጥ በፊት እጅን በሳሙና በደንብ መታጠብ፡፡ ፈሳሽን አብዝቶ መውሰድ ተቅማጥ እና ከፍተኛ ትኩሳት ስለሚኖር ውሀ በደንብ መውሰድ ነጭ ሽንኩርት በሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ ያደርጋል እንዲሁም ጎጂ መርዛማዎችን ለማስወገድ እና ፈጣን ፈውሶችን ለማስፋፋት ያግዛል በሶቢላ ባክቴሪያን የሚከላከሉ ፀረ-ባክቴሪያ እና አንቲባዮቲክ በውስጡ ይዞአል በተጨማሪ ትኩሳትን ይቀንሳል

መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com