የኩላሊት ጠጠር
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ

የኩላሊት ጠጠር ከጨው እና ጥቃቅን ንጥረ ነገሮች በሽንት ውስጥ የሚሰራ ሲሆን አንድ ላይ በመጣበቅ ጠጠር ይፈጥራል።
የጠጠሩ መጠን ከደቃቅ አሸዋ እስከ ጐልፍ ኳስ ሊተልቅ ይችላል። እነዚህ ጠጠሮች በኩላሊታችን ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ ወይም በሽንት ቧንቧ መስመሮች ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ።
የሽንት ስርዓት ሽንት ከመስራት ጀምሮ ከሰውነታችን እስከማስወገድ ድረስ ያለውን ሂደት ያጠቃልላል። የኩላሊት ጠጠር የሚፈጠረው በሽንት ውስጥ ያሉ የውሃ፣ ጨው፣ ንጥረነገሮችና ሌሎች ነገሮች ብዛት ሳይመጣጠን ሲቀር ነው።
የኩላሊት ጠጠር መንስኤ በቂ ውሃ አለመጠጣት ሲሆን በቂ የሆነ ውሃ መጠጣት የሽንታችን ቀለም ፈዛዛ የሆነ ቢጫ ወይም እንደ ውሃ ነጭ እንዲሆን ያደርገዋል ፡፡በዚህም መሠረት በቀን ከ 8-10 ብርጭቆ ውሃ እንድንጠጣ ይመከራል።
የኩላሊት ጠጠር በዘር የሚተላለፍበት አጋጣሚዎች አሉ ከቤተሰብዎ አባል ውስጥ ይህ በሽታ ያለበት ከሆነ እርስዎም የመያዝ ዕድል አለዎት።በደማቸው ውስጥ ከፍተኛ ዩሪክ አሲድ መጠን ያለባቸው ሰዎች በኩላሊት ጠጠር የመጠቃት እድል ይኖራቸዋል።
ከእርግዝና ጋር ተያይዘው የሚመጡ ለውጦች ለኩላሊት ጠጠር የማጋለጥ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ይኖራቸዋል ። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የፕሮጀስትሮን ሆርሞን መጠን በእርግዝና ወቅት ስለሚጨምር የሽንት ማጥ እንዲፈጠር ያደርጋል ፡፡
የበሽታው ምልክቶች፡- የኩላሊት ጠጠር በሚፈጠርበት ጊዜ ምንም ዓይነት የህመም ምልክት አይኖረውም እየቆየ ግን ጠጠሩ ከኩላሊት ወደ ሽንት ፊኛ በሚጓዝበት ጊዜ ከባድ ህመም ይከሰታል።
ከፍተኛ ህመም በጐን አካባቢ የሚሰማ ከሆነ ወይም የሽንት ቀለም ቀይ የሚመስል ከሆነ፣ እንዲሁም የሆድ ህመም፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ የሚኖር ከሆነ በአፋጣኝ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።
የኩላሊት ጠጠር ከኩላሊት ኢንፌክሽን ጋር ተጣምሮ በሚከሰትበት ጊዜ ትኩሳትና ብርድ ብርድ የማለት ምልክቶች ይታያሉ፡፡
በተጨማሪም ሽንት ለመሽናት መቸገር፣ ለመሽናት መቸኮል ወይም መጣደፍ ያስከትላል ።
ፈሳሽ ነገሮችን በበቂ ሁኔታ ባለመውሰድ የሚፈጠር የፈሳሽ እጥረት ወይም ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ በኋላ በላብ መልክ የወጣውን ፈሳሽ አለመተካት በኩላሊት ጠጠር የመያዝ ዕድሉን ይጨምራል ::
በሞቃታማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ለፈሳሽ እጥረት ስለሚጋለጡ በኩላሊት ጠጠር የመያዝ እድላቸው የሰፋ ነው።
ከኩላሊት ጠጠር ህክምና ምርመራዎች መካከል አንዱ ሲቲ ስካን ሲሆን ይህ ምርመራ በሽተኛውን ለጨረር ስለሚያጋልጥ አልትራሳውንድ ከኤክስ ሬይ ጋር አብረው ይታዘዛሉ።
በቤት ውስጥ የኩላሊት ጠጠርን ለማስወገድ የተረጋገጠ ህክምና ባይኖረውም በሽታው ጊዜ የሚሰጥና በራሱ ጊዜ በሽንት ቱቦዎች ወደ ሽንት ፊኛ ስለሚወርድ በቤት ውስጥ ሊወሰድ የሚገባው ህክምና ውሃ በብዛት መጠጣት ነው።
መጠናቸው ከ9-10 ሚሜ መጠን ያላቸው ጠጠሮች ያለ ምንም ህክምና በአጋጣሚ በራሳቸው ጊዜ ሊወጡ ይችላሉ።
በራሳቸው ጊዜ የማይወጡ የኩላሊት ጠጠሮች ሊቶትሪፕሲ ይሰራላቸዋል ፡፡ይህ ህክምና የዌቭ ንዝረትን በመጠቀም ትላልቅ ጠጠሮችን ወደ ትናንሽ ጠጠሮች መሰባበር ሲሆን ጠጠሮቹ በቀላሉ ከሽንት ጋር እንዲወጡም ያደርጋል ።
ሌሎች የህክምና ዘዴዎች ውጤታማ ካልሆኑ ቀዶ ጥገና በመስራት የኩላሊት ጠጠሩ ይወገዳል።
ነገር ግን የተለያዩ ህክምናዎችን ከማድረግ ይልቅ የሚመከረው ብዙ ውሃ በመጠጣት ማከም ነው፡፡
በሽንት የሚወጣውን ጠጠር በላቦራቶሪ ምርመራ በማድረግ ምን ዓይነት ጠጠር እንደሆነ በመለየት ለዚያ ችግር የተለየ መከላከያ መንገዶችን ለመውሰድ ይረዳል።
ከውሃ በተጨማሪ የሎሚ ጭማቂ መውሰድ የኩላሊት ጠጠርን ለመቀነስ ይረዳል።
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com