ስለ ልብ ህመም ምንያህል ያውቃሉ?
Author: admin
Date: 2021-04-16
ስለ ልብ ህመም ምንያህል ያውቃሉ?
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
የልብ በሽታ የሚባለው ማንኛውም በጤነኛ የልብ አሰራር ላይ ጣልቃ በመግባት አሰራሩን የሚያስተጓጉል ሁኔታ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል፡-
-በልብ ደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰተው ( Coronary artery)
-በልብ ጋኖች ባልቦላ ላይ የሚያጋጥመው (Valvular heart disease)
-በልብ ጡንቻዎች ላይ የሚያጋጥመው(Cardiomyopathy)
-በልብ ምት ላይ የሚፈጠረው መዛባት( Heart rhythm disturbances (arrhythmias)) -ከወሊድ በፊት በሚከሰት ምክኒያት የልብ ቅርፅ ችግር በሚወለዱ ሕፃናት ላይ የሚያጋጥም ሊሆን ይችላል፡፡
የልብ በሽታ ምልክት
-የደረት ህመም ወይም ውጋት
-የትንፋሽ ማጠር
-እግርና እና እጅ ላይ መቀዝቀዝ እና መድከም
-አንገት እና ጉሮሮ አካባቢ ህመም
-እራስን መሳት
-የልብ ምት መጨመር
-በሽታው በኢንፌክሽን ምክኒያት የተከሰተው ከሆነ ደግሞ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ትኩሳት እና ሳል ይኖራል፡፡
ለልብ በሽታ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
-እድሜ እየገፋ ሲሄድ
-ጾታ- ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ተጠቂ ናቸው፡፡ ሴቶች ደግሞ ካረጡ በኋላ የማጋለጥ እድላቸው ይጨምራል
-በዘር በሚተላለፍ
-ለጨረር ወይም ለኬሞቴራፒ (የካንሰር ህክምና) ተጋልጠው ከነበረ
-ማጨስ
-አመጋገብ
-የደም ግፊት
-ከፍተኛ ኮሌስትሮል
-ስኳር
-ውፍረት
-እንቅስቃሴ አለማድረግ
-ጭንቀት
የልብ በሽታ ለመከላከል
-የደም ግፊት፣ስኳር እና ኮሌስተሮልን መቆጣጠር
-አለማጨስ
-እንቅስቃሴ ማድረግ
-አመጋገብን ማስተካከል
-ውፍረት መቀነስ
-ጭንቀት ማስወገድ
የልብ በሽታ ህክምና እንደየ ችግሩ አይነት ይለያያል፡፡
የልብ ውጋትን እንዴት ልናስታግስ እንችላለን
የቀጠጥና ስር ፈጭቶ ከኑግ ጋር መብላት ፣ የመርዝ ተቀፅላ በአፍንጫ ማሽተት እንዲያስነጥስ ይረዳል ፣ የጦስኝ ቅጠል ውሃውን አፍልቶ በባዶ ሆድ መጠጣት እና ዝንጅብል ፣ ጥቁር አዝሙድ እና ነጭ ሽንኩርት በአንድ ላይ ፈጭቶ በሻይ መውሰድ ከበሽታው ለማገገም የሚረዱን የቤት ውስጥ መፍትሄዋች ናቸው፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com