የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለማስታገስ የሚረዱ የህክምና ዘዴዎች ክፍል ሁለት
Author: admin
Date: 2021-04-15
የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለማስታገስ የሚረዱ የህክምና ዘዴዎች ክፍል ሁለት
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ኮሮና ቫይረስ ጉንፋን መሰል ገዳይ በሽታ ከተከሰተ ግዜ አንስቶ የብዙሀንን ህይወት የነጠቀ እና እየነጠቀ ያለ አደገኛ በሽታ እንደሆነ የሚዘነጋ አይደለም ፡፡
ሆኖም ይህ ገዳይ በሽታን ከስሩ ለማጥፋት የሚያስችል መድሀኒት ባይኖርም ቀደም ሲል ለጉንፋን ፣ ለኢንፉሌንዛ ፣ ለሳል ወዘተ .. ለመሳሰሉት የነበረንን ሀገራዊ ብልሀት በአግባቡ መልሰን ልንጠቀም ይገባል፡፡
ከዚህ ቀጥለው ያሉት ምክሮች ስንጠቀም መንግስት በየግዜው የሚነግረንን መመሪያዎች ወደጎን ትተን ሊሆን አይገባም ፡፡
የመከላከያ ዘዴዎች
የጤናዳም ቅጠል ፣ አሪቲ ፣ ነጭ ሪያን ቅጠል ፣ የሴጅ ቅጠል ፣ የባህር ዛፍ ቅጠል ቀንበጡን ፣ የሎሚ ቀንበጥ ፣ የአጁባን ቅጠል ፣ የደማከሴ ቅጠል ፣የአርቲሚሲያ ቅጠል ፣ የላቬንደር ቅጠል ፣ የናና ቅጠል እና የታጌታስ ቅጠል በአንድ ለይ አፍልቶ መታጠን ፡፡
ሌላው ምግብ ከተመገብን በኋላ ወይም ከመመገብ በፊት ጥርስንም ሆነ ምላስን በሚገባ ማፅዳት ፣ አፍን በሎሚ ፍንካች በቀን ሁለት ግዜ ማፅዳት ፣ አፍንም ሆነ ጉሮሮን በቀን ሁለት ግዜ በጨው መጉመጥመጥ ፣ የዝንጅብል ፍንካች ማኘክ እና በጤናዳም እንጨት ጥርስን መፅዳት ቫይረሱን ለመከላከል ከሚረዱን ዘዴዎች መካከል በጥቂቱ ይህን ይመስላሉ ፡፡
የኮሮና ቫይረስ ገዳይ በሽታ ስለሆነ እራሳችንን እንጠብቅ መንግስት የሚሰጠንን መመሪያዎች ችላ አንበል !!!!!
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com