የአጥንት ካንሰር
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ

የአጥንት ካንሰር ጤነኛ የአጥንት ህዋሳትን በማጥፋት ጤነኛ ያልሆኑ ህዋሶች ከመጠን በላይ በመባዛት የአጥንት ያለአግባብ እብጠት እንዲኖር የሚያደርግ ህመም ነዉ፡፡
ከአጥንት ህዋሳት የሚጀምር የአጥንት እብጠት ዋናዉ የአጥንት ካንሰር(Primary bone cancer)የሚባል ሲሆን ከጡት፣ከሳንባ እና ከማህጸን የሚዛመት ደግሞ ከሌሎች ብልቶች የሚመጣ ካንሰር (Metastatic) ይባላል፡፡
የአጥንት ካንሰር አይነቶች
ኦስቲዮሳርኮማ፡-
ይህ አደገኛዉ እና በስፋት የሚታየዉ የካንሰር አይነት ነዉ፡፡ብዙ ጊዜ እድሜያቸዉ ከ10 እስከ 25 አመት በሆናቸዉ ላይ የሚከሰት ነዉ፡፡ በዋናነት የእጅ እና የእግር አጥንቶች ላይ እንዲሁም ህጻናት ፈጣን እድገት በሚያሳዩባቸዉ የቁርጭምጭሚት እና ጫንቃ አካባቢዎች ላይ ይከሰታል፡፡
የኤዊንግስ እድገት፡-
በጣም አደገኛ እና እድሜያቸዉ ከ4 እስከ 15 ያሉት ላይ በብዛት ይስተዋላል፡፡በእጅ እና እግር ረጃጅም አጥንቶች የመካከለኛዉ ክፍል አካባቢ የመታየት እድል አለዉ፡፡
ኮንድሮሳርኮማ፡-
በመከሰት አቅሙ ከኦስቲዮሳርኮማ ቀጥሎ ሁለተኛ ሲሆን እድሜያቸዉ ከ40 በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ይከሰታል፡፡የዚህ እብጠቶች የሚነሱት ከአጥንት ለስላሳ አካላት ረቂቅ ህዋሳት ሲሆን በአንጻራዊነት እድገታቸዉ በዝግታ ሆኖ አደገኞች ናቸዉ፡፡በአብዛኛዉ የዳሌ አጥንትን የሚያጠቃ ሲሆን ወደ ሳንባ እና ብሽሽት ሊዛመት ይችላል፡፡
ማሊግናንት ፋይብረስ ሂስቲዮሳይቶማ፡-
ይህ አይነት ካንሰር በአብዛኛዉ ጡንቻ እና ጅማትን በማጥቃት ይታወቃል፡፡እድሜያቸዉ ከ50 እስከ 60 አመት ባሉ ሰዎች ላይ ይከሰታል፡፡
ለአጥንት ካንሰር አጋላጭ ሁኔታዎች
የታሽጉ ምግቦችን እና መጠጦችን አብዝቶ መጠቀም
የጨረር ህክምና
ሌሎች የሰዉነት ክፍሎች ላይ ካንሰር
አንድ አንድ የካንሰር መድሐኒቶች
በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ካለ
የአጥንት ካንሰር ምልክቶች
ችግሩ የተከሰተበት አጥንት የህመም ስሜት
ችግሩ የተከሰተበት አጥንት ላይ እብጠት እና የመደንዘዝ ስሜት
ከፍተኛ የድካም ስሜት
ያልታሰበ የክብደት መቀነስ
የአጥንት ካንሰር ህክምና
የአጥንት ካንሰር ህዋሳትን የመግደል አቅም ስላላቸዉ በቫይታሚን ኤ የበለጸጉ ምግቦች እንደ ፓፓያ፣ማንጎ፣ካሮት፣ ጎመን፣ ሰላጣ፣ ስጋ፣ እንቁላል፣ አሳ፣ ወተትና የወተት ተዋዕጾ መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡
የጸሐይ ብርሀን በበቂ ሁኔታ ማግኘት
የኬሞቴራፒ ህክምና
የጨረር ህክምና
በሰዉነት ዉስጥ በቂ የደም ዝዉዉር እንዲኖር ለማድረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
መልካም ጤንነት!!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com