የወፍ በሽታ የምታሲዘው የለሊት ወፍ ትሆን?
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
እናንተም ብዙ ሰምታችሁ ይሆናል..... የወፍ በሽታ በተለምዶ የለሊት ወፍ ሸንታበት ነው ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን ህክምናውም ወፏን መመገብ እንደመድሀኒትነት ይጠቅማል እየተባለ ይነገራል።
ስንቶቻችሁ ናችሁ በዚህ በሽታ ተይዛችሁ የምታውቁ? ስንቶቻችሁ ናችሁ ከአገር ለመውጫ ምርመራ ወድቃችሁ መውጣት ያቃታችሁ? ስንቶቻችሁ ናችሁ በዚ በሽታ የሞተ ወዳጅ ያላችሁ? ስንቶቻችሁ ናችሁ ባህላዊ መድሀኒት የተጠቀማችሁ? የወፍ በሽታ ወይም ሄፓታይተስ የሚባለው A,B,C,D,E ተብለው
ሚከፈሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ስለ ሄፓታይተስ ኤ (hepatitisA) ተብሎ ስለሚጠራው በሽታ ትንሽ እንበላችሁ ። ሄፓታይተስ ኤ ሁሉን የማህበረሰብ ክፍል የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን በብዛት በህፃናት ላይ ይታያል።
መተላለፊያ መንገዶች
ቫይረሱ በበሽታው ከተለከፉ ሰዎች አይነምድር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ዋነኛ መተላለፊያው መንገድ ከሰው ወደ ሰው ቫይረሱ በምራቅ ንክኪ (በምግብ ሰአት) በሰገራ ንክኪ የተበከለ ምግብ እና ውሀ
ከንፈር ለከንፈር መሳሳም ሲሆኑ እነዚህን ማወቅ ለመከላከል ይጠቅመናል።
ምልክቶች
ትኩሳት
የምግብ የፍላጎት ማጣት
ማቅለሽለሽና ማስታወክ
ድካም
አይን ቢጫ መሆን
ቆዳ ቢጫ መሆን የመሳሰሉት ናቸው።
ሄፓታይተስ A ቫይረስ ኢንፌክሽን በህጻናት ላይ ከተከሰተ በአጭር ግዜ ውስጥ ምልክት የሚያሳይ ሲሆን ጥቂት ቀናቶችን ከቆየ በሃላም የሚጠፋ ህመም አይነት ነው፡፡ ሕክምናው ምን ይመስላል እንዴትስ ህመሙ እንዳይከሰት መከላከል እንችላለን?
መከላከያ ዘዴዎች
የምግብ ሳህን መለየት
ከሽንትቤት መልስ እጅ መታጠብ
ሄፓታይተስ A ኢንፌክሽን ለመዳን ብዙን ጊዜ ከሁለት ሳምንት እስከ ወራት እድሜ ሊወስድ ይችላል በአጠቃላይ ግን የህጻኑ ዕድሜ እየቀነሰ በሚመጣበት ጊዜ ለመዳን የሚወስድበት ጊዜ አጭር እንደሚሆን ጥናቶች ያመላክታሉ:: ህመሙ በሚከሰትበት ወቅት በፕሮቲን ይዘት ከፍ ያሉ የምግብ አይነቶችን(ለምሳሌ ሰጋ) የጉበት ስራን ላለመጨመርና ህመሙን ላለማባባስ ሲባል ማቆም ያስፈልጋል ይሁንና ጣፋጭ ምግቦችን ግን መመገብ ይመከራል
• የመልቲ ቫይታሚን B ኮምፕሌክስ መድሃኒቶችም የመዳን ሂደቱ ላይ ጠቀሜታ ይኖራቸዋል
• ታማሚው ህጻንም ከህመሙ እስኪያገግም ድረስ እረፍት ማድረግ ይኖርበታል።
ህጻናት ህመሙ ከተከሰተ እስከ አንድ ሳምንት ግዜ ድረስ ህመሙን ስለሚያስተላለፉ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ አይመከርም። ሆኖም ግን ከአንድ ሳምንት በኅላ ታማሚው በሽታውን የማያስተላልፍ ሲሆን እራሱም በድጋሚ አይያዝም:: ሌላው ደግሞ ወቅቱን የጠበቀ ክትባት ህጻናት እንዲወስዱ ማድረግ ነው፡፡
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com