የጆሮ ደግፍ
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
የጆሮ ደግፍ በመፕስ ቫይረስ አማካይነት የሚከሰትና የምራቅ እጢዎችን በተለይ የፓሮቲድ የምራቅ ዕጢን በብዛት የሚያጠቃ የህመም አይነት ነዉ፡፡
የህመሙ ምልክቶች:
የተወሰኑ ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኃላ ምንም የህመም ምልክት አሊያም መጠነኛ የሆነ ምልክት ሊያሳይ ይችላሉ፡፡የህመሙ ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት ታማሚዉ በቫይረሱ ከታያዘ/ለቫይረሱ ከተጋለጠ/ ከ2 እስከ 3 ሳምንታት በኃላ ነዉ፡፡ የህመሙ ምልክቶች
• በአንዱ ወይም በሁለቱም ከጆሮ ዝቅ ብሎ ባለዉ የፊት ክፍል እብጠትና ህመም መከሰት
• ትኩሳት
• የራስ ምታት
• የጡንቻ ላይ ህመም
• ድካምና ምቾት ያለመሰማት
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• ምግብ ሲያላምጡ/ሲያኝኩ/ ወይም ሲዉጡ ህመም መሰማት
የህመሙ ምክንያቶች:
የጆሮደግፍ መፕስ በሚባል የቫይረስ አይነት የሚከሰት ሲሆን ከሰዉ ወደ ሰዉ በምራቅ ድሮፕሌት/ቅንጣት/ በቀላሉ የሚተላለፍ ነዉ፡፡ለህመሙ ክትባት ወስደዉ የማያቁ ከሆነ በጆሮ ደግፍ የተያዘ ሰዉ በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ወቅት ወደ አየር ቫይረሱን ስለሚረጨዉ እርስዎ ያንን የተበከለ አየር ሲምጉት በቀላሉ እንፌክሽኑ ሊይዝዎት ይችላል፡፡በተጨማሪም እንደ ሳህን ወይም ኩባያ/ብርጭቆ ያሉ እቃዎችንንም በጋራ መጠቀም ህመሙ እንዲተላለፍ ያደርጋል፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች:
የጆሮ ደግፍ በቫይረስ አማካይነት የሚመጣ ስለሆነ ፀረባክቴሪያዎችን መዉሰድ ምንም ጥቅም የለዉም፡፡ ህመሙ በህፃናትም ይሁን በአዋቂዎች ላይ በሁለት ሳምንታት ዉስጥ በራሱ ጊዜ ሊድን የሚችል ነዉ፡፡ አንድ ሰዉ በህመሙ ከተያዘ ከሳምንት በኃላ ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰዉ ሊያስተላልፍ ስለማይችል ወደስራም ሆነ ወደ ትምህርት መመለስ ይችላል፡፡
የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና
• እረፍት ማድረግ
• የታመመዉን ሰዉ ወይም ህፃን ለተወሰኑ ቀናት መለየት፡- ይህ ቫይረሱ ወደ ሌላ ሰዉ እንዳይዛመት ይረዳል፡፡ከላይ እንደተገለፀዉ ቫይረሱ የህመም ምልክቶቹ ከመታየታቸዉ ከ 3 ቀናት በፊት ጀምሮ ህመሙ ከታየ በሃላ ለአንድ ሳምንት ያህል ከታማሚዉ ወደ ጤነኛዉ ሰዉ ይተላለፋል፡፡
•ያለሃኪም ትእዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን መዉሰድ
• ሞቅ ያለ ወይም ቀዝቃዛ ነገር እብጠቱ ላይ መያዝ
• ብዙ መታኘክ የሚፈልግ ምግብ ያለመመገብ፡- ይልቁኑ ለስለስ ያሉ ምግቦችን አሊያም ሾርባ ነክ ምግቦችን መመገብ
• የሚጎመዝዙ/የሚኮመጥጡ ምግቦችን ያለመመገብ፡- አነዚህ ምግቦች ምራቅ እንዲበዛ ስሊሚያደርጉ ህመሙ እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡ለምሳሌ ሎሚ፣ ብርቱካንና የመሳሰሉት
• ፈሳሽ በብዛት መጠጣት
ልጅዎ የጆሮ ደግፍ ካለዉና የሚከተሉት ምልክቶች ከታዩ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ
• ትኩሳት፡- ከ39 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ከሆነ
• መጠጣትና መመገብ ካልቻለ
• የመዘባረቅ ባህሪ ካመጣ
• የሆድ ህመም ካለዉ
• ወንዶች ላይ የዘር ፍሬዉ ማበጥና ህመም ካለዉ
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com