የደም መርጋት በምን ይከሰታል፣ እንዴትስ እንከላከለው?
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
አሁን አሁን አሳሳቢ የሆነው የደም መርጋት ችግር የየእለት እንቅስቃሴዎቻችንን መነሻ በማድረግ እንደመከሰቱ መንስዔዎቹ እጅግ በርካታ መሆናቸው ነው የሚነገረው።
በዋናነት ግን የደም አጓጓዥ በሆኑትና "ብለድ ቬዝል" የተሰኙት የደም ክፍሎች ግድግዳ ላይ በሚደርስ ጉዳት የሚከሰት ነው።
ጉዳቱ በአይን የሚታየውና እንደ መቆረጥ ያለው አደጋ ሲደርስ የሚከሰት ሲሆን፥ አልያም በአይን የማይታይ ይሁንና በደም ሴሎቻችን ላይ የሚደርሱ አደጋዎችንም ይጨምራል።
በተጨማሪም ደም በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት መዘዋወሩን ሲያቆም የደም መርጋት እክል ሊከሰት እንደሚችል ነው የሚነገረው።
ወይም በተለያዩ በሽታዎች መነሻነት ደም ሊረጋ ይችላል።
የደም መርጋት አይነቶች፦
1.ቬነስ ትሮምቦሲስ
የዚህ አይነቱ የደም መርጋት ጡንቻዎች ደምን ወደልብ መግፋት ሲሳናቸው የሚከሰት ነው ።
በዚህም መንቀሳቀስ ያልቻለው ደም በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ወደ ጠጣርነት መቀየር ሲጀምር የደም መርጋት ይከሰታል።
የደም መርጋቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ከሆነም ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ልብ የሚደርሰው ደም ሊቆም ይችላል።
ለዚህ ጥሩ ማሳያ ምሳሌ የሚሆነው እንደልብ የማይንቀሳቀስ ወንዝ ላይ በጊዜ ሂደት የሚፈጠሩት እንደ አልጌ እና አረም የመሳሰሉት ነገሮች በወንዙ ላይ መከማቸት በመጀመር ውሃው እንዳይንቀሳቀስ ይገድቡታል።
በሂደትም አረሞቹ እጅብ ብለው በመብቀል የውሃውን አንስተኛ ግፊት በመቋቋም ጉዞውን እስከመግታት ይደርሳሉ።
2.አርተሪያል ትሮምቦሊ
ሌላኛውና .አርተሪያል ትሮምቦሊ የተሰኘው የደም መርጋት አይነት ደግሞ በተለያዩ ሆኔታዎች ሊፈጠር የሚችል ነው።
የደም ቧንቧ መጥበብ (atherosclerotic disease) የደም መርጋትን ከሚያስከትሉ ምክንያቶች የሚጠቀስ ሲሆን፥ከዚህ በተጨማሪም ለተያያዥ የጤና እክሎችም እንደሚዳርግ ነው የሚነገረው።
የደም ቧንቧ መጥበብ እንደ የልብ ህመም፣ ስትሮክና ለተያያዥ ህመሞች እንድንጋለጥ ያደርጋል።
ለደም መርጋት ችግር የሚዳርጉ ነገሮች፦
• ሲጋራ ማጨስ
• ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን ማዘውተር
• የደም ዝውውርን ለማስተካከል የሚደረግ ቀዶ ህክምና
• የልብ ህመም
• የልብ ምት መዛባት(በተለያዩ የጤና እክል ሊከሰት ይችላል) ናቸው።
የደም መርጋት ችግር በአብዛኛው ሰው ሰራሽ በሆነ ሁኔታ እንደመከሰቱ፥ የአመጋገብ እና የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል እንዲሁም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማዘውተር ልንከላከለው እንችላለን።
መርጋት
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736