አደንዛዥ እፅ መጠቀም የሚያመጣው ጉዳት
ቅዱስሚካኤልየባህልህክምና
ሀኪምሰለሞንአዳሙ


የአደንዛዥ እፅ ሱስ ማለት አንድ ሰው ራሱን መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ የሱስ አምጭ ንጥረ ነገሮችን ለመውሰድ ፍላጎት ሲያድርበት እና ችግር የሚያስከትሉ እንደሆነ እያወቀ እነዚህን ንጥረ ነገሮች ሲወስድ ነው፡፡ አደንዛዥ እፆች የሰዎችን ሀሳብ፤ ስሜት፤ እንቅልፍ፤ የምግብ ፍላጎት እና ማህበራዊ ግንኙነትን ይቀይራሉ፡፡
በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ሃገራት ይህን አእምሮን የሚያነቃቁ አደንዛዥ እፆች የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር በአስገራሚ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ከአደንዛዥ እፅ ጋ ተያይዘው በሚከሰቱ ችግሮች ዋነኛ ተጠቂ ከሆኑት አገሮች አንዷ ስትሆን በማህበረሰብ ጤና ችግር መካከልም የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀም ዋናው ጉዳይ እየሆነ መጥቷል፡፡
አእምሮን የሚያነቃቁ አደንዛዥ እፆች በሚወሰዱበት ጊዜ በዋናነት አእምሮ ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር በአካላዊና ስነልቦናዊ ተግባሮች ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡ ብዙ ሰዎች የአደንዛዥ እፅ በሚፈጥረው የአእምሮ መነቃቃት እና አመለካከት ለውጥ በመደሰት ይዝናኑበታል፡፡ በመጨረሻም ይህ በመሆኑ ሰዎች ሳያውቁት በተደጋጋሚ በመውሰድ ወደ ልምድ ወይም ሱስ ውስጥ ይገባሉ፡፡
ከዚህ ቀጥለን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን የአደንዛዥ እፆች፤ የሚያስከትሉትን ችግሮች፤ ቀድሞ መረዳትና የህክምና እርዳታ ስለመፈለግ እንዲሁም እንዴት ሰዎች እንዚህን ንጥረ ነገሮች ከመጠቀም እንዲጠበቁ ወይም እንዳይጠቀሙ ማድረግ እንደሚቻል ፅሁፉ ያትታል፡፡
የአልኮል መጠጥ
ከገጠር እስከ ከተማ በባሕላዊ መንገድ ከሚዘጋጁት ጠላ፣ ጠጅ፣ እና አረቄን ጨምሮ በዘመናዊ መልክ እስከሚዘጋጁት ድራፍት፣ ቢራ፣ ጅን ፤ውስኪ እና ሌሎችም የአልኮል መጠጥ ዓይነቶች ሲሆኑ የአልኮል መጠጥ በሁሉም የአገራችን ክፍል እንደሚጠጣ ይታወቃል፡፡ የአልኮል መጠጥ ሱስ ከሚያስይዙ ንጥረ-ነገሮች አንዱ ነው፡፡
የአልኮል ተጠቃሚዎች አልኮል መጠጥን የመጠቀሚያ ምክኒያቶች
• ለጊዜ ማሳለፊያነት
• በጓደኛ ተፅዕኖ
• ለጊዜያዊ ደስታ
• በአዕምሮ ህመም ምክንያት እና ለሎቹም
የአልኮል መጠጥ እና ጉዳቶቹ
ምንም እንኳን የአልኮል መጠጥ በብዙዎቹ ዘንድ ለጊዚያዊ ደስታ እና ጊዜ ማሳለፊያነት ቢዝወተርም የአልኮል መጠጥ አዝወትረው በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የአካል እና የአይምሮ ጤና ጉዳት፣ የማህበራዊ ኑሮ እና የኢኮኖሚ ችግሮችን ያስከትላል፡፡
የአልኮል መጠጥ በአእምሮ ጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት
¨ የድብርት በሽታ
¨ የጭንቀት በሽታ
¨ የመርሳት በሽታ
¨ ስንፈተ ወሲብ
¨ የእንቅልፍ መዛባት
¨ ለፀብ መዳረግ
የአልኮል መጠጥ በአካላዊ ጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት
የአልኮል መጠጥ አዘውትረው በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ
የሚከተሉት የጤና ችግሮች ይታይባቸዋል
• የጉበት፣ የልብ፣ የደም ቧንቧ፣ የጨጓራ በሽታ እና ለሞት መዳረግ
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• የቁም ቅዠት
• የደም ግፊት መጨመር
• በሽታን የመከላከል አቅም መቀነስ
• ከጠጪ እናቶች የሚወለዱ ሕጻናት ላይ የአእምሮ እድገት ውስንነት ማስከተል
• አልኮልን አብዝቶ መጠጣት የመወሰን ችሎታን በማዛባት ላልተገባ እና ልቅ ለሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት በመዳረግ ለኤች አይ ቪ እና ለአባላዘር በሽታዎች መከሠት እንዲሁም መዛመት ምክንያት መሆን
በማሕበራዊ ኑሮ ላይ የሚያደርሰው ችግር
በአልኮል መጠጥ ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮች በተጠቃሚው ላይ ብቻ ተወስነው የሚቀሩ ባለመሆናቸው በቤተሰብ እና በማሕበረሰቡ ላይ የሚከተሉትን ከፍተኛ ችግሮች ያስከትላል፡፡
• የአልኮል መጠጥ የሚጠጡ ወላጆች ለልጆቻቸው መጥፎ አርአያ ይሆናሉ
• ለትዳር መፍረስ እና ለቤተሰብ መበተን ምክንያት ይሆናል
• ልጆች ወደ ጎዳና እንዲወጡ ምክንያት ይሆናል፡፡
• ማሕበራዊ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ ያደርጋቸዋል
• የግል እና የአካባቢ ንፅህናን ያለመጠበቅ ያስከትላል
• የአካባቢን ፀጥታ እና ሠላም ያውካል
• ለህግ እና ደንብ አለመገዛት
በኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት
• አልኮል አዝወትረው መጠጣት የግለሰቡን ብሎም የቤተሰቡን ኪስ ያራቁታል
• የስራ ብቃት እና ተነሳሽነትን በማዳከም ምርታማነትን ይቀንሳል
• በመጠጥ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች እና ችግሮችን ለማከም የሚወጣው ወጪ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡
የአልኮል መጠጥ በድንገት ማቆም የሚያስከትላቸው ችግሮች
የአልኮል ሱስ ችግር ያለባቸው ብዙ ሰዎች አልኮል በሚያቆሙበት ጊዜ ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ የሚደርሱ ችግሮች ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ ከእነዚህም ችግሮች ውስጥ የእጅ መንቀጥቀጥ፣ ማላብ፣ የእንቅልፍ ሰዓት መዛባት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና ማቅለሽለሽ ይጠቀሳሉ፡፡ በአብዛኛዉ እነዚህ ምልክቶች ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውሰጥ በራሳቸው መንገድ ወይም በህክምና እርዳታ ሊወገዱ የሚችሉ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ አልኮልን በድንገት በማቆም ዴሊርየም ተሬመንስ የተባለ ችግር ሊከሰት ይችላል፡፡
የዚህ አይነት ችግር መገለጫዎቹም የቁም ቅዠት ራስን መሳት ወይም መቆጣጠር አለመቻል፣ አለመረጋጋት፣ የመረበሽ ስሜት፣ መንቀጥቀጥ፣ አካባቢን፤ ሰዎችንና ጊዜን መለየት አለመቻል፣ ከፍተኛ ትኩሳትና ላብ፣ ከእውነታ የራቀ እይታ (ለሌሎች ሰዎች የማይታይን ነገር አየሁ ማለት) እና ፍርሃት ናቸው፡፡ ምልክቶቹም መጠጥ ካቆሙ በኋላ ከ 3 እስከ 5 ባሉት ቀናት ዉስጥ የሚከሰቱ ናቸው፡፡
እነዚህን ችግሮች ለማስቀረት የሚቻለው የአልኮል ሱስ ተጠቂው ግለሰብ አልኮል ለማቆም ሲወስን ለጤና ባለሙያ በማማከር ተገቢ የሆነ የህክምና ድጋፍ እንዲደረግለት በመጠየቅ ነው።

• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736