የቶንሲልን ህመም በቤት ውስጥ ለማከም
Author: Hakim Solomon
Date: 2021-03-03
የቶንሲልን ህመም በቤት ውስጥ ለማከም
ቅዱስሚካኤልየባህልህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
የቶንሲል ህመም/ቶንሲል በቶንሲል መቆጥቆጥ ምክንያት የሚከሰት ነዉ፡፡ ብዙዉን ጊዜ የቶንሲል ህመም የሚከሰተዉ በቫይረስ እንፌክሽን ሲሆን በባክቴሪያ ኢንፌክሽንም ሊመጣ ይችላል፡፡
የቶንሲል ህመም ምልክቶች
የቶንሲል ህመም በብዛት የሚያጠቃዉ ህፃናትን ሲሆን የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡
• የቶንሲል መቅላትና እብጠት
• የቶንሲል መከርከር
• ምግብ በሚዉጡበት ወቅት ህመም መኖር/ መዋጥ መቸገር
• ትኩሳት
• በአንገት ላይ ያበጡና ህመም ያላቸዉ ዕጢዎች መከሰት
• የድምፅ መቀየር
• መጥፎ የአፍ ሽታ
• የሆድ ህመም( በተለይ በእድሜያቸዉ ትናንሽ ህፃናት ላይ)
• የአንገት ህመም/መጠንከር
• የራስ ምታት ናቸዉ፡፡
በጣም ጨቅላ በሆኑ ህፃናትና የህመማቸዉን ሁኔታ መግለፅ በማይችሉ ህፃናት ላይ
• ሲዉጡ ህመም ስላላቸዉ የምራቅ/ለሃጭ መዝረከርክ
• ምግብ መመገብ እምቢ ማለትና
• ያልተለመደ ድካም የህመሙ ምልክቶች ናቸዉ፡፡
የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?
• በ24 ሰዓታት ዉስጥ ለዉጥ የሌለዉ የቶንሲል ህመም ካጋጠመዎ
• ምግብ ሲዉጡ ህመም ካለዎና
• የድካም/የመዝለፍልፍ ስሜቶች ከፍ ያለ ከሆኑ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡
ለቶንሲል ህመም የሚያጋልጡ ነገሮች
• ለጋ እድሜ፡- የቶንሲል ህመም ትናንሽ ህፃናትንና ለጋ እድሜ ላይ ያሉ ልጆችን በብዛት ያጠቃል፡፡
• በተደጋጋሚ ኢንፌክሽኑን ለሚያመጡ ጀርሞች መጋለጥ፡- በትምህርት ቤት የሚዉሉ ህፃናት ከአቻዎቻቸዉ ጋር ያላቸዉ የቀረበ ግንኙነት/ንክኪ ለቫይረሶችና ባክቴሪያዎች በቀላሉ እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል፡፡
የቶንሲል ህክምና
1. የቤት ዉስጥ ህክምና
የቶንሲል ህመሙ በቫይረስም ይሁን በባክቴሪያ ምክንያት ቢከሰትም የቤት ዉስጥ ህክምናዎችን መከወን ምቾት እንዲሰማዎና ቶንሲሉ ቶሎ እንዲድን ያደርገዋል፡፡ የቶንሲል ህመሙ የተከሰተዉ በቫይረስ መሆኑ ከተረጋገጠ የህክምና ባለሙያዎ ምንም ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒት ስለማያዝልዎ ህመሙ እንዲድን የቤት ዉስጥ ህክምና ማከናወን የህክምናዉ ዋናዉ አካል ነዉ፡፡ የቶንሲል ህመም በ10 ቀናት ዉስጥ ሊሻሻል ይችላል፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ የቤት ዉስጥ ህክምናዎች
• በቂ እረፍት ማግኘት፡- ብዙ ያለማዉራትና በቂ እንቅልፍ ማግኘት
• ፈሳሽ በበቂ መጠን መዉሰድ
• ምቾትን ሊሰጡ የሚችሉ ምግቦችን መመገብ፡- ትኩስ ፈሳሾች እንደ ሾርባ፣ካፊን የሌለዉ ሻይ፣ የሞቀ ዉሃ በማር እንዲሁም ቀዝቃዛ የሆኑ እንደ በረዶ ያሉ ነገሮች የጉሮሮ መከርከርን ሊያክሙ ይችላሉ፡፡
• ጨዉ ባለዉ ዉሃ አፍን መጉመጥመጥ
• ወደ ዉስጥ የሚገባዉን አየር እርጥበታማ/ሂሙድፋይ እንዲሆን ማድረግ፡- ወይ የቀዝቃዛ አየር ሂሙድፋየር መጠቀም አለዚያ ደግሞ እንፋሎት መታጠን ደረቅ አየር ጉሮሮ ላይ የሚያመጣዉን መከንከን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡
• ሊቆጠቁጡ የሚችሉ ነገሮችን ማስወገድ፡- ጉሮሮን ሊከረክሩ ከሚችሉ እንደ የሲጋራ ጭስና የቤት ማጽጃ ኬሚካሎች እራስን መጠበቅ
• ህመምና ትኩሳት ካለ ማስታገሻ መዉሰድ፡- እንደ ፓራሲታሞላና አይቡ ፕሮፌን ያሉ መድሃኒቶችን መጠቀም፡፡
2. መድሃኒቶች
የቶንሲል ህመም የተከሰተዉ በባክቴሪያ ኢንፌክሽን ከሆነ የግድ ፀረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶችን (አንቲባዮቲክሶችን) መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡ በህክምና ባለሙያዎ የታዘዘልዎትን መድሃኒት በአግባቡ ወስዶ መጨረስ የሚያስፈልግ ሲሆን በአግባቡ ካልተወሰደ ግን ባክቴሪያዉ ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰራጭ፤ህፃናት ላይ ደግሞ የልብ ህመም እንዲከሰት መንስኤ መሆንና ቀጣይነት ያለዉ የቶንሲል ህመም (ክሮኒክ ቶንሲላይትስ) እንዲከሰት ያደርጋል፡፡
የቶንሲል ህመምን መከላከል
ቶንሲልን ሊያመጡ የሚችሉ ጀርሞች (ባክቴሪያና ቫይረስ) ከሰዉ ወደ ሰዉ ተላላፊ ናቸዉ፡፡ ስለሆነም የቶንሲል ህመምን ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች ዉስጥ ዋነኛዉ የግል ንፅህናን መጠበቅ ነዉ፡፡ እራስዎም ሆኑ ልጆችዎ
• ምግብ ከመመገባችሁ በፊትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጃችሁን በደንብ መታጠብ
• የመጠጫና መመገቢያ እቃዎችን በጋራ ያለመጠቀም ይመከራል፡፡
ልጆች የቶንሲል ህመም ካላቸዉ ኢንፌክሽኑን ወደሌሎች እንዳያዛምቱ
• ልጅዎ ታሞ ከሆነ ለተወሰነ ቀናት እቤት እንዲቆይ ማድረግ
• ልጅዎ መቼ ት/ት ቤት መሄድ እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማማከር
• ልጅዎ በሚስልበትና በሚያስነጥስበት ወቅት አፍና አፍንጫዉን በሶፍት ወይም በክርኑ የዉስጠኛዉ ክፍል እንዲሸፍን ማስተማርና
• ልጅዎ ካሳለዉ ወይም ካስነጠሰዉ በኃላ እጁን/እጇን እንዲታጠቡ ማስተማር ናቸዉ፡፡
በባህላዊ ህክምና የሚመከሩ የቶንሲል ሀክምናዎች
• የዘርጭ እምቧይ የበሰለውን ፍሬ በመጭመቅ ፋሬውን ለይቶ ካወጡ በኋላ ጥጥ በቀጭን እንጨት ላይ ጠምጥሞ ፋሳሹን እየነከሩ የጉሮሮ ቀኝ እና ግራዉን በደንብ ማፅዳት በቀን ሁለት ግዜ በየስድስት ሰአት ልዩነት
• የነጭ ሽንኩርት እና የዝንጅብል ሻይ ከምግብ በኋላ በቀን ሶስት ግዜ መጠጣት
• ነጭ ሽንኩርት ከፈጩ በኋላ ለብ ባለ ውሃ መጉመጥመጥ
• ነጭ ሽንኩርት በሎሚ ውሃ በቀን ስድስት (6) ግዜ መጉመጥመጥ
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736