ሱፍ ለጤና የሚሰጠው ጠቀሜታ
ቅዱስሚካኤልየባህልህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ

ከቅባት እህል ከሚመደበው ሱፍ ምን የጤና ጠቀሜታ እናገኝ ይሆን?
የሱፍ ተክል ዓመቱን በሙሉ ልናገኘው የምንችለው እና በርካታ የጤና ጥቅሞችን ሊያስገኝልን የሚችል የቅባት እህል ነው።
ብዙዎቻችን በተለይ የሱፍ ፍትፍትን ለብቻውም ሆነ በተለምዶ በየአይነቱ በምንልው የምግብ ዝርዝር ላይ እንደ አይነት ጨምረን እንመገበዋለን።
ይሁንና ሱፍ ከምናስበው በላይ በርካታ ጥቅሞችን ለሰውነታችን እንደሚያበረክትስ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?
እኛም ታዲያ ሱፍ ለጤናችን ከሚያበረክታቸው እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች መካከል የተወሰኑትን ለማየት ወደድን፦
1.ካንሰርን ይከላከላል፣
ሱፍ ሴሊኒየም የተባለው ንጥረነገር መገኛ እንደመሆኑ መጠን የሰውነት ህዋስ (ሴል) ጉዳትን በመከላከል ለካንሰር እንዳንጋለጥ ያግዛል፣
2.ለአጥንት ጥንካሬ፣
ሱፍ ከካልሲየም ውጪ ለአጥንት ጥንካሬ ጠቃሚ የሆኑ ማዕድናትም መገኛ ነው።
ካልስየም፣ ማግንዚየም፣ ኮፐርን የመሳሰሉ ማዕድናትን በውስጡ በመያዙም ለአጥንታችን ጤንነት እና ጥንካሬ ተመራጭ ነው።
በተጨማሪም ሱፍ ቫይታሚን ኢ በውስጡ ስለሚገኝ ከአተነፋፈስ ጋር ለተያያዙ ህመሞች ፍቱንነቱ ይነገርለታል።
3.ጭንቀትን ያስወግዳል፣
በሱፍ ውስጥ የምናገኘው የማግኒዚየም ማዕድን የነርቭ ስርዓትን የማነቃቃት ባህሪ ስላለው በቀላሉ ለጨንቀት እንዲሁም ለከባድ የራስ ምታት እንዳንጋለጥ ያግዛል።
4.ለንፁህ እና አንፀባራቂ ቆዳ፣
በሱፍ ውስጥ በበቂ መጠን የምናገኘው ቫይታሚን ኢ ፥ ዩ ቪ ሬይስ የተሰኘው እና በቆዳ ላይ ጉዳት የሚያደርሰውን የጨረር አይነት በመከላከል እንዲሁም ቆዳችንን በማሳመር ማራኪ ቆዳ እንዲኖረን ያስችላል።
5. በሰውነት ውስጥም ሆነ ውጪ የማቃጠል ስሜትን ለመግታት፣
በሰውነት ውስጥም ሆነ ውጪ የሚከሰትን የማቃጠል ስሜት ለመግታት፣ በመገጣጠሚያ አካላት ላይ የሚደርስ ህመምን ለማስቆም እና ለጨጓራ ህመም መፍትሄው አሁንም ሱፍን አዘውትሮ መመገብ ነው።
6.የልብ ህመምን ለመከላከል፣
በቀን ከግማሽ ኩባያ ያነሰ ሱፍን ከምግብ ገበታችን ዝርዝር ውስጥ በማካተት ጎጂ የኮሌስትሮል መጠንን ከደም ቧንቧችን ላይ እንዲወገድ በማድረግ የልባችን ጤንነት በእጅጉ እንዲጠበቅ ማድረግ እንችላለን።

• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736